Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የደስታዬ ምንጭ

Yedestayie Mench

2004 · ትራክ 8 · 5:19 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አልቅበዘበዝም ከዚህ ወደዚያ

ደስታን ልፈልገው ከኢየሱስ ወዲያ

ያ መቅበዝበዜ ፈጽሞ ያቆመው

ኢየሱስ ጌታዬን ያገኘሁት ቀን ነው (፪x)

በቃ (፫x) መቅበዝበዜ አከተመ እዚያ ጋር

ኢየሱስ ነው የደስታዬ ምንጭ ኢየሱስ ነው (ኢየሱስ ነው) (፪x)

ኢየሱስ ነው የሰላሜ ምንጭ ኢየሱስ ነው (ኢየሱስ ነው) (፪x)

በጸሎት ፊቱ?? ደስ ላሰኘን

በሃዘን ፈንታ ደስታን ከሰጠኝ

የምን ማቀቅር አንገት መድፋት ነው

ሃዘን ለጠላት ለእኔ ደስታ ነው

ፈጽሞ አይከፋኝ ቤቱ መጥቼ

የሰላሙን/የደስታውን ምንጭ እርሱን አግኝቼ (፪x)

ኢየሱስ ነው የደስታዬ ምንጭ ኢየሱስ ነው (ኢየሱስ ነው) (፪x)

ኢየሱስ ነው የሰላሜ ምንጭ ኢየሱስ ነው (ኢየሱስ ነው) (፪x)

ጌታን ላመልከው ቤቱ ከመጣሁ

አላማ ብዬ ጊዜዬን ከሰዋሁ

ማኩረፌ ይቅር የልብ ሃዘኔ

እዚህ ቁጭ ብዬ በሃሳብ መሄዴ

ይልቅ ልደሰት ላክብረው ታዲያ

ውስጤ ያለው ነው ሃሌሉያ (፪x)

ሃሌሉያ (፬x) ሃሌሉያ (፬x) ሃሌሉያ (፬x) ሃሌሉያ (፬x)

ሃሌሉያ (፬x) ሃሌሉያ (፬x) ሃሌሉያ (፬x) ሃሌሉያ (፬x) (ኦ ሃሌሉያ)

ሃሌሉያ (፬x) ሃሌሉያ (፬x) ሃሌሉያ (፬x) ሃሌሉያ (፬x) (ኦ ሃሌሉያ)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ