ይነጋል
Yenegal
2004 · ትራክ 5 · 5:38 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
መልካም እረኛዬ ኢየሱስ
ምሥጋናዬ ይሄው (፪x)
አንተ ስላለኸኝ ለምን እሰጋለሁ
ይነጋል እላለሁ ፣ ይነጋል
ቁጥር 1 · Verse 1
በጊዜው ነገር ላይ ዐይኖቼን አልጥልም
ቀኑ በሎ??? እዛ ላይ እንደመሸ አይቀርም
የገባችው ፀሐይ መውጣቷ ለማይቀር
ዝምብዬ ላመስግን ሌቱን ሳልሻገር
አዝማች · Chorus
መልካም እረኛዬ ኢየሱስ
ምሥጋናዬ ይሄው (፪x)
አንተ ስላለኸኝ ለምን እሰጋለሁ
ይነጋል እላለሁ ፣ ይነጋል
ቁጥር 2 · Verse 2
አይደለሁም አይደለሁም ብቸኛ
አብሮኝ ሚሄድ አለ
አይዞህ አይዞህ የሚል
በርታ ትደርሳለህ (፪x)
በከበረ አሰራር ቤቱን ሰሮቶናል
በፀጋው ስጦታ ውስጤን ሞልቶታል
የክብሩን ቤት እርሱ ማክበር ስለሚያውቅ
ይኑርብኝ እንጂ ለምን ልጨነቅ
ወጀቡ ቢበዛም መልካም እያየሁ ነው
በዶት የተኛ ይህን ከየት አገኘው
ጌታ ተገልጦልኝ ብዙ ተምሬያለሁ
ብኞአል ያልኩህ ሁሉ ፈጽማለሁ
አይደለሁም አይደለሁም ብቸኛ
አብሮኝ ሚሄድ አለ
አይዞህ አይዞህ የሚል
በርታ ትደርሳለህ (፪x)
አዝማች · Chorus
መልካም እረኛዬ ኢየሱስ
ምሥጋናዬ ይሄው (፪x)
አንተ ስላለኸኝ ለምን እሰጋለሁ
ይነጋል እላለሁ ፣ ይነጋል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ