Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አቤቱ አምላኬ

Abietu Amlakie

2013 · ትራክ 3 · 6:25 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አቤቱ አምላኬ ከፍ አደርግሃለሁ

ደግሜ ደግሜ ክብርን እሰጥሃለሁ (፪x)

የማይገባኝን እኔን ያስወደደህ

በመስቀል ላይ ሞተህ ነፍስህን ለእኔ ሰጠህ

መቼ ይረሳኛል ሁሌ አስበዋለሁ

ጌታ ሆይ ከፍ በል አመሰግናለሁ

አቤቱ አምላኬ ከፍ አደርግሃለሁ

ደግሜ ደግሜ ክብርን እሰጥሃለሁ (፪x)

በማይለወጥ ፍቅር እኔን ወደኸኛል

ለክብርህ እንዳጥን አንተ መርጠኸኛል

ሳልሰለች ጠዋት ማታ አንተን አመልካለሁ

ለዘለዓለሙ ክብርን እሰጥሃለሁ

አቤቱ አምላኬ ከፍ አደርግሃለሁ

ደግሜ ደግሜ ክብርን እሰጥሃለሁ (፪x)

በእኔ ዘንድ ያለ በአንተ ዝንድ የሌለ

ያለ ነገር ቢኖር እሰጥህ ነበረ

አንተ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ነህ

ለውለታህ ምላሽ ምሥጋና ለሥምህ

አቤቱ አምላኬ ከፍ አደርግሃለሁ

ደግሜ ደግሜ ክብርን እሰጥሃለሁ (፪x)

አስብህና እደሰታለሁ ጌታ ኢየሱስ ሆይ እወድሃለሁ

አስብህና እደሰታለሁ የደስታዬ ምንጭ እወድሃለሁ

አስብህና እፎይ እላለሁ የእረፍቴ እወድሃለሁ

አስብህና እኔ እርፋለሁ የእረፍቴ እወድሃለሁ

አስብህና እደሰታለሁ የደስታዬ ምንጭ ወድሃለሁ

አስብህና እደሰታለሁ ጌታ ኢየሱሴ እወድሃለሁ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ