የአምላኬ ቃል አያረጅም
Yeamlakie Qal Ayarejem
2013 · ትራክ 2 · 5:37 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በማይሆን መንገድ ስራመድ
አልፌም ስንገዳገድ
ቃልህ ነው መካሪዬ
ቃልህ ነው መላሼ
አልፎ ስንት ዘመን
ገስግሶ ስንት ዓመት
አልተለወጠም ሕያው ነው
አይለወጥም ፅኑ ነው
የቃልህ ፍቺ ያበራል
አልተለወጠም ዛሬም ይሰራል
ዘለዓለም ይኖራል እያበራ
ከሚያምኑት ጋራ
አዝማች · Chorus
የአምላኬ ቃል አያረጅም
የኢየሱስ ቃል አያረጅም
ዘለዓለም ይኖራል እያበራ
ከሚያምኑት ጋራ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከዘመን በፊት ብዙ ኖሯል
ዛሬም ዘመኑን ይቀድማል
ለነፍስ ይዘምራል ለነፍስ ይናገራል
ለእስረኛው መፈታት ነው
ለጨለማው ንጋት
መፍትሄ አለው ለሁሉም
መልስ ነው ለሚሰሙ
በአዋቂዎች ዕውቀት ብዛት
አያውቀውም እርሱ መረታት
ዘለዓለም ይኖራል እያበራ
ከሚያምኑት ጋራ
አዝማች · Chorus
የአምላኬ ቃል አያረጅም
የኢየሱስ ቃል አያረጅም
ዘለዓለም ይኖራል እያበራ
ከሚያምኑት ጋራ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሆሆሆሆ ሆሆሆሆ
የቃልህ ጉልበቱ የቃልህ ውበቱ
በዘመን መካከል ይገርማል ጽናቱ
ዘለዓለም ይኖራል እያበራ
ከሚያምኑት ጋራ
ሰርክ አዲስ ነው ከቶ አይሰለችም
ቢደገም ቢደገም ከቶ አይጠገብም
ዘለዓለም ይኖራል እያበራ
ከሚያምኑት ጋራ
በአዋቂዎች ዕውቀት በሊቃውንት ብዛት
ይረታል እንጂ አያውቅም መረታት
ዘለዓለም ይኖራል (፫x)
ዘለዓለም ይኖራል እያበራ ከሚያምኑት ጋራ
ዘለዓለም ዘለዓለም ዘለዓለም
ዘለዓለም ይኖራል
ዘለዓለም ዘለዓለም ዘለዓለም ዘለዓለም ይኖራል
ዘለዓለም ይኖራል
በማይሆን መንገድ ስራመድ
አልፌም ስንገዳገድ
ቃልህ ነው መካሪዬ
ቃልህ ነው መላሼ
አልፎ ስንት ዘመን
ገስግሶ ስንት ዓመት
አልተለወጠም ሕያው ነው
አይለወጥም ጽኑ ነው
የቃልህ ፍቺ ያበራል
አልተለወጠም ዛሬም ይሰራል
ዘለዓለም ይኖራል እያበራ
ከሚያምኑት ጋራ
አዝማች · Chorus
የአምላኬ ቃል አያረጅም
የኢየሱስ ቃል አያረጅም
ዘለዓለም ይኖራል እያበራ
ከሚያምኑት ጋራ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ