ከባሕር ይዘልቃል
Kebaher Yezelqal
2013 · ትራክ 6 · 5:59 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጥቂቱን የሰው ፍቅር ዓይኔ አይቶ ሲደነቅ
የፍቅር መጀመሪያው አንተማ እንዴት ትልቅ
ጥቂቱን የሰው መውደድ ዓይኔ አይቶ ሲደነቅ
የፍቅር ጅማሬው አንተማ እንዴት ትልቅ
አዝማች · Chorus
ከባሕር ይዘልቃል እህህህህህ
የፍቅርህ ጥልቀቱ እሆሆሆሆ
ራስህን አሳንሰህ ገብተሃል በየቤቱ
ቁጥር 2 · Verse 2
ከባሕር ይዘልቃል እህህህህህ
የፍቅርህ ጥልቀቱ እሆሆሆሆ
በኢየሱስ በኩል መጥተህ ተገኘህ በየቤቱ
አቤት ፍቅር (፬x)
አቤት መውደድህ (፬x)
ወደድኩህ ወደድኩሽ ያለው ቃላትን እየቆለለ
ሳይታሰብ በድንገት ከስፍራው ገለል አለ
በቆላ ሆነ በደጋ በክረምትም በበጋ
ሕያው ነው የአንተስ ፍቅር ይለወጥ ብዬ አልሰጋ
አዝማች · Chorus
ከባሕር ይዘልቃል እህህህህህ
የፍቅርህ ጥልቀቱ እሆሆሆሆ
ራስህን አሳንሰህ ገብተሃል በየቤቱ
ቁጥር 3 · Verse 3
ከባሕር ይዘልቃል እህህህህህ
የፍቅርህ ጥልቀቱ እሆሆሆሆ
በኢየሱስ በኩል መጥተህ ተገኘህ በየቤቱ
አቤት ፍቅር (፬x)
አቤት መውደድህ (፬x)
አንተ መልካም መልክህ
ሁኔታ የማይለውጥህ
ነገር የማይለውጥህ
ዘመን የማይለውጥህ
መልካም መልካም መላካም (፪x)
ፍቅርህ ዘለዓለማዊ ቸርነትህ ዘለዓለማዊ
አንተ ሆይ አመሰግንሃለሁ
ደግ ሆይ አመሰግንሃለሁ
ቸር ሆይ እቀኝልሃለሁ
ቸር ሆይ እገዛልሃለሁ
ጥቂቱን ሰው በጐነት ዓይኔ አይቶ ሲቸገር
የበጐነት መጀመሪያው አንተማ እንዴት ትልቅ
ጥቂቱን የሰው ቸርነት ዓይኔ አይቶ ሲደነቅ
የቸርነት መደምደሚያው አንተማ እንዴት ትልቅ
አዝማች · Chorus
ከባሕር ይዘልቃል እህህህህህ
የፍቅርህ ጥልቀቱ እሆሆሆሆ
ራስህን አሳንሰህ ገብተሃል በየቤቱ
ቁጥር 4 · Verse 4
አቤት ምህረትህ (፬x)
አቤት ተዕግስትህ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ