Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኧረ በረከቱ

Ere Bereketu

2013 · ትራክ 7 · 7:34 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እንዳለፈ ውኃ መከራዬን አስረሳኝ (፪x)

እንደ ጠዋት ፀሐይ ሕይወቴን አበራው (፪x)

እንደ ቀትር ደግሞ አደመቀው እንደገና (፪x)

ኧረ እንደው (፪x) ምን ይሻለኛል

ዝም ብሎ እግዚአብሔር ይባርከኛል ፣ ይባርከኛል (፪x)

ኧረ በረከቱ ገደብ አጣ (፬x)

አዎ ለማዕበሉ ገደብ አለው

ለወጀቡ ገደብ አለው

ለመከራው ገደብ አለው

ግን ለበረከቱ ገደብ የለው (፬x)

እኔ ዝም ብዬ ሳመልክህ

እኔ ዝም ብዬ ሳከብርህ

እኔ ዝም ብዬ ስወድህ

እኔ ዝም ብዬ ስሰጥህ

የሰማያትንም መስኮቶች ከፈትክና (፫x)

በረከትን አወረድከው እንደገና (፫x)

እንደገና (፬x)

ኧረ በረከቱ ገደብ አጣ (፬x)

እንዴት ብዬ ላሳያችሁ

ድንቅ እኮ ነው አምላካችሁ (፫x)

እርሱ እኮ ነው የሞላው

በመስፈሪያው ሰፈረው

ነቀነቀውና ጨቆነው (፬x)

ይባርካል እጁ ያጠግባል

የልብንም መሻት ሁሉ ይሰጣል

የላይኛውን እና የታችኛውን ምንጪ

ሌላ ማን ይሰጣል እግዚአብሔር ነው እንጂ (፪x)

አዎ ለሀዘኑ ገደብ አለው

ለለቅሶውም ገደብ አለው

ለጭንቀቱም ገደብ አለው

ለእንቆቅልሽ ገደብ አለው

ለችግሩ ገደብ አለው

ለማጣቱ ገደብ አለው

ለበሽታው ገደብ አለው

ግን ለበረከቱ ገደብ የለው (፮x)

ኧረ በረከቱ ገደብ አጣ (፮x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ