በተቀደሰው
Beteqedesew
2013 · ትራክ 8 · 6:03 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በተቀደሰው መቅደስህ
ከፍ ባለው ዙፋንህ ላይ
ያለመናወጥ ጸንተህ የምትኖር
አንተ ብቻ እኮ ነህ አምላኬ ሆይ
በተቀደሰው መቅደስህ
ከፍ ባለው ዙፋንህ ላይ
ያለመናወጥ ጸንተህ የምትኖር
አንተ ብቻህን ነህ ጌታዬ ሆይ
ቁጥር 1 · Verse 1
የቱ ገብቶኝ የቱንስ አውቄ
እንዳስተዋይ ራሴን መነቅነቄ
የአንተን ክብር የአንተን ማንነት
ማን ተረድቶት ማን አስተውሎት
ብሞክርም በቃልህ ገልጸህ
ከቶ አልችልም እንዲህ ልልህ
ያለኝ ቋንቋ በቃ ይህ ነውና
እግዚአብሔር ልበልህ ገናና
አዝማች · Chorus
በተቀደሰው መቅደስህ
ከፍ ባለው ዙፋንህ ላይ
ያለመናወጥ ጸንተህ የምትኖር
አንተ ብቻ እኮ ነህ አምላኬ ሆይ
በተቀደሰው መቅደስህ
ከፍ ባለው ዙፋንህ ላይ
ያለመናወጥ ጸንተህ የምትኖር
አንተ ብቻህን ነህ ጌታዬ ሆይ
ቁጥር 2 · Verse 2
በማይታይ ብርሃን የደመቀው
መኖሪያህ በላይ በሰማያት ነው
ለዘለዓለም በቅዱሱ ስፍራ
የምትኖር ደግሞ እየተፈራህ
በስልጣንህ ሁሉን የምትገዛ
ባለግርማ ሞገስህ የበዛ
ሁሉህ ከእግርህ በታች ተገዝቶልህ
ያለመናወጥ አንተ ትኖራለህ
አዝማች · Chorus
በተቀደሰው መቅደስህ
ከፍ ባለው ዙፋንህ ላይ
ያለመናወጥ ጸንተህ የምትኖር
አንተ ብቻ እኮ ነህ አምላኬ ሆይ
በተቀደሰው መቅደስህ
ከፍ ባለው ዙፋንህ ላይ
ያለመናወጥ ጸንተህ የምትኖር
አንተ ብቻህን ነህ ጌታዬ ሆይ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሁሉም ነገር ጊዜ አለው ሰዓት
ለመውደቁ ወይ ለመነሳት
ከፀሐዯ በታች አለው ሁሉ
በየተራ ይፈራረቃሉ
ተቀያሪ ተለዋጭ የሌለህ
ትናንትናም ዛሬም ያው አንተ ነህ
አይደፈር ዙፋን ወንበርህ
እግዚአብሔር የዘለዓለም ነህ
አዝማች · Chorus
በተቀደሰው መቅደስህ
ከፍ ባለው ዙፋንህ ላይ
ያለመናወጥ ጸንተህ የምትኖር
አንተ ብቻ እኮ ነህ አምላኬ ሆይ
በተቀደሰው መቅደስህ
ከፍ ባለው ዙፋንህ ላይ
ያለመናወጥ ጸንተህ የምትኖር
አንተ ብቻህን ነህ ጌታዬ ሆይ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ