ተመሥገን የምለው
Temesgen Yemelew
2013 · ትራክ 10 · 5:50 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሁሌ ሲነጋ ሲመሽም ተመስገን የምለው
ለምን እንደሆን ቢጠየቅ ምክንያቴ ብዙ ነው
ብቻ እኔ እስካለሁኝ ድረስ ወይ እርሱ እስኪመጣ
ክብር ውዳሴ ምሥጋኔ ከአፌ አይታጣ ሆሆ
ከአፌ አይታጣ ፤ ከአፌ አይታጣ ሆሆ ፤ ከአፌ አይታጣ (፪x)
ማለዳ እህህህ ማለዳ አሃሃሃ
ዝማሬ መልካም ነው ለጌታ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ዝማሬን በአፌ አንተ ጨምረሃል
ነውር የሌለበት መሷዕት ይገባሃል
በእጄ ንጽህና በከንፈሬ ቃል
እንዳመሰግንህ ፍቃድህ ሆኗል
በመንፈስህ ደስታ በቃልህ መከር
እሄው ዝማሬዬ ክብርህን ይናገር (፪x)
አዝማች · Chorus
ሁሌ ሲነጋ ሲመሽም ተመስገን የምለው
ለምን እንደሆን ቢጠየቅ ምክንያቴ ብዙ ነው
ብቻ እኔ እስካለሁኝ ድረስ ወይ እርሱ እስኪመጣ
ክብር ውዳሴ ምሥጋኔ ከአፌ አይታጣ ሆሆ
ከአፌ አይታጣ ፤ ከአፌ አይታጣ ሆሆ ፤ ከአፌ አይታጣ
ማለዳ እህህህ ማለዳ አሃሃሃ
ዝማሬ መልካም ነው ለጌታ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ኪሩቤል ሱራፌል አንተን ያከብራሉ
ለታላቅነትህ አንተን ያከብራሉ
ንጹሁን አምልኮ ለአንተ ያቀርባሉ
አንዱ ለአንዱ ያወራል የፊትህን ግርማ
ይህንን ሲያደርጉ አይታክቱምና አይሰለቹምና
አዝማች · Chorus
ሁሌ ሲነጋ ሲመሽም ተመስገን የምለው
ለምን እንደሆን ቢጠየቅ ምክንያቴ ብዙ ነው
ብቻ እኔ እስካለሁኝ ድረስ ወይ እርሱ እስኪመጣ
ክብር ውዳሴ ምሥጋኔ ከአፌ አይታጣ ሆሆ
ከአፌ አይታጣ ፤ ከአፌ አይታጣ ሆሆ ፤ ከአፌ አይታጣ
ማለዳ እህህህ ማለዳ አሃሃሃ
ዝማሬ መልካም ነው ለጌታ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ