አፍ አለው አምላኬ
Af Alew Amlakie
2013 · ትራክ 9 · 7:23 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አፍ አለው አምላኬ እርሱ ይናገራል
እኔ ዝም እላለሁ በስራው ይከብራል
እጅ አለው አምላኬ ሁሉን ሰው ይረዳል
አምኖ ለተጠጋው ደካማን ይወዳል
አምላኬ ጆሮ አለው ለቅሶዬን ይሰማል
የእምነት ጸሎቴን ሁሉን ይፈጽማል
ዓይን አለው አምላኪ እሁሉን ነገር ያያል
የራሱ ለሆኑት ዘወትር ይታደጋል
ቁጥር 2 · Verse 2
ክንዱ ጠንካራ ነው አምላኬ ሲረዳ
መንጥቆ ያወጣል ከመከራ ጓዳ
አምላኬ ሲቆጣ እጁን ሲዘረጋ
ሁሉን ይቀበላል የስራውን ዋጋ
ቃሉ እጅግ ኃያል ነው የሰው ልብ ያቀልጣል
መራራውን ጣፋጭ አርጐ ይለውጣል
አምላኬ ሲቆጣ በጅራፍ ይቀጣል
የምድረበዳውን አውሬ ያናውጣል
ቁጥር 3 · Verse 3
ጻድቅ ነው አምላኬ በጽድቅ ይበይናል
ፍርድን አያጣምም ጥም ፍርድን ይፈርዳል
ፊት አይቶ አያዳላ ለወገኔ አይል
ከዚህ ይልቅ ለዚያ ብሎ ማያታልል
በጽድቅ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ይፈርዳል
ፍርድ ለጠመመበት ምላሹን ይሰጣል
እንደአምላኬ ያለ ትክክል ማን አለ
ከምድር ፈራጆች የላቀ የተሻለ
ቁጥር 4 · Verse 4
አምላኬ ድምጽ አለው ለልብ ይናገራል
ሃሳብና ስራንም ይመረምራል
ነፍስና መንፈስን መዝኖ ሲጠግን
አምላኬ ሃኪም ነው የሰውን ልብ ሲያድን
ሁሉም በእጁ ነው ሁሉም በፍቃዱ
አምላኬ ሕያው ነው ወደ ሌላ አትሂዱ
አዝማች · Chorus
ይህን ታላቅ ጌታ ላስተዋውቃችሁ
አምላኬ ኢየሱስ ነው ይሁን አምላካችሁ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ