Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በልቶና ጠጥቶ

Beltona Teteto

2013 · ትራክ 4 · 6:35 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አንድ ፊት አለ እኔ የለመድኩት

ማልጄ ልየው እንደናፈቅሁት

ቀና ይሆናል ይሰምራል ቀኔ

የወዳጄን ፊት ካየሁት እኔ (፪x)

በልቶና ጠጥቶ መኖር ሕይወት እንዳልሆነ ከገባኝ ሰንብቶ

እግዚአብሔር እግዚአብሔር ሚያሰኝ አንዳች ነገር ውስጤ ገብቶ

በልቶና ጠጥቶ መኖር ሕይወት እንዳልሆነ ከገባኝ ሰንብቶ

አባቴን አባቴን ሚያሰኝ አንዳች ነገር ውስጤ ገብቶ

ሌላውማ አያምረኝም እኔ የኢየሱስ ነኝ (፪x)

እኔ የኢየሱሴ ነኝ (፬x)

የሕይወት ብቸኛ ቁም ነገር

የሆንከው ወዳጄ እግዚአብሔር

የሆንከው ጌታዬ እግዚአብሔር

በህልውናህ ውስጥ መኖር

መታደል ነው ትልቅ ክብር (፪x)

በልቶና ጠጥቶ መኖር ሕይወት እንዳልሆነ ከገባኝ ሰንብቶ

አባቴን አባቴን ሚያሰኝ አንዳች ነገር ውስጤ ገብቶ

ሌላውማ አያምረኝም እኔ የኢየሱስ ነኝ (፪x)

እኔ የኢየሱሴ ነኝ (፬x)

የእኔ ሞገስ የእኔ ተስፋ

ነፍሴ እንደ አንተ የወደደችው ጠፋ

ነፍሴ እንደ አንተ የአፈቀረችው ጠፋ

አንተን ባየሁበት ዓይኔ

አልታይ አለኝ ሌላው እኔ (፪x)

በዚህ በምድር ላይ ማጣት የማልፈልገው

ሌላ ነገር አይደለም አምላኬ ሆይ አንተን ነው (፪x)

በልቶና ጠጥቶ መኖር ሕይወት እንዳልሆነ ከገባኝ ሰንብቶ

አባቴን አባቴን ሚያሰኝ አንዳች ነገር ውስጤ ገብቶ

ሌላውማ አያምረኝም እኔ የኢየሱስ ነኝ (፪x)

እኔ የኢየሱሴ ነኝ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ