ተነስ
Tenes
2013 · ትራክ 5 · 5:17 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዓይኖችህ ተገልጠው ብታይ
ማን እንዳለ ከአንተ ጋር
ይገባህ ነበረ የተገዛህበት ዋጋ
በውስጥህ ያለው ኢየሱስ ሕያው ነው
የተናገረውን ሊያደርግ በቃሉ የታመነ ነው
አዝማች · Chorus
አታውቅም ወይ የፈጠረህን
አታውቅም ወይ ሁሌ እንደሚያይህ
አታውቅም ወይ እንደሚሰማህ
አታውቅም ወይ ለአንተ እንደሚራራ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጥያቄ በበዛበት ዓለም ብትኖር
ምታየው ምትሰማው ሚያታልል ቢመስል
ኢየሱስ ከኃጢአት መቀር ተፈትኖ አልፏል
ልብህን ስጠው ሊረዳህ ተዘጋጅቷል
አዝማች · Chorus
አታውቅም ወይ የፈጠረህን
አታውቅም ወይ ሁሌ እንደሚያይህ
አታውቅም ወይ እንደሚሰማህ
አታውቅም ወይ ለአንተ እንደሚራራ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አንተ ታናሽ መንገድ
ፍጻሜህ ያማረ ነው
የመረጠህ ኢየሱስ በቃሉ የታመነ ነው
ጠቢብም ሚያደርግህን ቃል ብላና
ጐዳናህንም ደግሞ በእርሱ አንጻና
ወንጌሉን ይዘህ ተከተለው
ከግብ ሊያደርስህ የታመነ ነው
ተነስ (፪x)
ወንድሜ ሆይ ተነስ ተነስ (፪x)
ተነስ ተንተ ሂድ
ተነስ ወንድሜ ሆይ
ተነስ ሆሆሆሆ ተነስ
ሆሆሆሆ ህምምምም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ