ፀሎቴ
Tselotie
2013 · ትራክ 11 · 5:21 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ስፀልይ ነፍሴ ይነቃቃል
ስፀልይ እንባዬም ይደርቃል
ስፀልይ ሁሌ እበረታለሁ
ስፀልይ ኃይልን አገኛልሁ
ስፀልይ ቋጠሮ ይፈታል
ስፀልይ መዝጊያው ይከፈታል
ስፀልይ ሁሌ እጽናናለሁ
ስፀልይ እረፍት አገኛለሁ
ስፀልይ ዲያቢሎስ ይወድቃል
ስፀልይ ስፍራውን ይለቃል
ስፀልይ ድልን አገኛለሁ
ስፀልይ ሀሴት አደርጋለሁ
ስፀልይ ቃሉን እረዳለሁ
ስፀልይ አስተውለዋለሁ
ስፀልይ እምነት እሞላለሁ
ስፀልይ ሁሌ እደሰታለሁ
ለአንድ ክርስቲያን በኢየሱስ ለዳነ
የዘለዓለምን ሕይወትን ላገኛ
ጸሎት ትልቁ ዋና ለሕይወቱ
ትልቁ ነገር ነው እኮ ቁልፉ
ጸሎት ትልቁ ዋና ለሕይወቱ
ትልቁ ነገር ነው እኮ ቁልፉ (፪x)
ስኖር ከጌታ ጋር በዚህች ምድር ላይ
እንዴት ሳልጸልይ የሱን ፊት ሳላይ
ድምጼን ሳሰማው ድምጹን ሲያሰማኝ
ጸሎት ብቻ ነው ሁሌ ያስተማረኝ
ድምጼን ሳሰማው ድምጹን ሲያሰማኝ
ጸሎት ብቻ ነው ለእኔ ያስተማረኝ (፪x)
በቃሉ ነግሮኝ ወደ እኔ ጩህ ብሎ
መልስ እንዲሰጠኝ በእራሱ ምሎ
እኔም በፊቱ ተንበረከኩኝ
ታላቅ እንዳለኝ አንድ ነገር አየሁኝ
በሬን ዘግቼው በስውር ለምኜው
በግልጽ ከፍሎኛል ጌታን ታምኜው (፪x)
አዝማች · Chorus
ስፀልይ ነፍሴ ይነቃቃል
ስፀልይ እንባዬም ይደርቃል
ስፀልይ ሁሌ እበረታለሁ
ስፀልይ ኃይልን አገኛልሁ
ስፀልይ ቋጠሮ ይፈታል
ስፀልይ መዝጊያው ይከፈታል
ስፀልይ ሁሌ እጽናናለሁ
ስፀልይ እረፍት አገኛለሁ
ስፀልይ ዲያቢሎስ ይወድቃል
ስፀልይ ስፍራውን ይለቃል
ስፀልይ ድልን አገኛለሁ
ስፀልይ ሀሴት አደርጋለሁ
ስፀልይ ቃሉን እረዳለሁ
ስፀልይ አስተውለዋለሁ
ስፀልይ እምነት እሞላለሁ
ስፀልይ ሁሌ እደሰታለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ