አቤቱ አንተ
Abietu Ante
2004 · ትራክ 4 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አቤቱ አቤቱ አቤቱ
አንተ ለዘላለም ልዑል ነህ
አቤቱ አቤቱ አቤቱ
ኢየሱስ ለዘላለም ጌታ ነህ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንደ ብዙ ውሆች ድምጽህ ያስፈራል
ፊት ህ ያበራል ያንፀባርቃል
ክብርህን አይቶ ማንስ ይቆማል
ኢየሱስ አንተን ማን ይመስልሃል (፪x)
አዝማች · Chorus
አቤቱ አቤቱ አቤቱ
አንተ ለዘላለም ልዑል ነህ
አቤቱ አቤቱ አቤቱ
ኢየሱስ ለዘላለም ጌታ ነህ
ቁጥር 2 · Verse 2
ዝናህን ሰምቼ ከሩቅ መጥቻለሁ
እንቆቅልሼንም ከእግርህ ስር ጥያለሁ
ከሰማሁት በላይ ሆነህ አግኝቼሃለሁ
ኤልሻዳይ መሆንህን ይኸው አይቻለሁ
አዝማች · Chorus
አቤቱ አቤቱ አቤቱ
አንተ ለዘላለም ልዑል ነህ
አቤቱ አቤቱ አቤቱ
ኢየሱስ ለዘላለም ጌታ ነህ
ቁጥር 3 · Verse 3
ዙፋንህ ያስፈራል የእሳት ነበልባል ነው
ግርማ ሞገስ ህም ጌታዬ ልዩ ነው
የክብርህ ጸዳል እጅጉን ያበራል
በፊት ህ ለመቆም ከቶ ማን ይችላል
አዝማች · Chorus
አቤቱ አቤቱ አቤቱ
አንተ ለዘላለም ልዑል ነህ
አቤቱ አቤቱ አቤቱ
ኢየሱስ ለዘላለም ጌታ ነህ
ቁጥር 4 · Verse 4
ባለ ዝና ነህ ባለ ሞገስ
አንተ ታላቅ ነህ ዛሬም ንጉሥ
በዘመናት ድንቅ የምትሰራ
እግዚአብሔር አንተ ገናና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ