Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እግዚአብሔር ወዶናል

Egziabhier Wedonal

2004 · ትራክ 10 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እግዚአብሔር ወዶናል

በጽድቁ ጠርቶናል (፪x)

አፍቅሮናል (፰x)

አብ ላንድያ ልጁ ፈፅሞ ሳይራራ

አሳልፎ ሰጠው ልጁን ለመከራ

የፍቅሩ ብዛት ስፋቱ ርዝመቱ

ተገልጦ አይተናል በኢየሱስ ምህረቱ (፰x)

ዘላለም ላይጠላን አንድ ጊዜ ወዶናል

ከእጁ ሊያወጣን ኧረ ማን ይችላል

ፍቅሩ ለዘላለም ጽኑና ቋሚ ነው

ጊዜና ሁኔታ ዘመን የማይሽረው (፰x)

አስጨናቂያችንን ከእግራችን ሥር ጥሎ

አከበረን ጌታ በአብ ቀኝ አስቀምጦ

በነፃነት ልንኖር አርነት ወጥተናል

ከሰይጣን ባርነት ቀንበር አምልጠናል (፰x)

እግዚአብሔር ወዶን ከሰማይ አሰበን

ከጥፋት ሊያድነን ልጁን ወደ እኛ ሰደደ (፪x)

በአሰራርህ ተደስተናል

አመራረጥህ እጅግ ገርሞናል

ልዩ ነው ፍቅርህ አሃሃ

ልዩ ነው ፍቅርህ ኦሆሆ (፪x)

ፍጥረት ያምልክህ አሃሃ

ፍጥረት ያምልክህ ኦሆሆ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ