ከአንተ ወዴት
Keante Wediet
2004 · ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከአንተ ወዴት እንሄዳለን ጌታ
ከአንተ ወዴት እንሄዳለን (፪x)
አንተኮ የሕይወት ቃል አለህ (፬x)
ካንተ ፍቅር አለብን (፫x)
ለዘላለም አንለይም አንተን
ታዲያ ጌታ ሆይ እንዴት እንሆናለን
ኑሮ ካንተ ውጭ ምን ጣዕም ይገኛል
የሕይወታችን ጨው ቅመም አንተ ነህ
ሰው ያደረገን ለኛ ሰው ሆነህ (፭x)
በቃልህ ተመክረን ወግ ማዕረግ አይተናል
የምትለው ሁሉ እጅግ ተስማምቶናል
በፍቅርህ ነፍሳችን ዛሬም ተይዛለች
ያለ ኢየሱሴ አይሆንም ትላለች (፪x)
አዝማች · Chorus
አንተ ታዋጣናለህ ጌታ ታዋጣናለህ
አንተ ታዛልቃለህ ኢየሱስ የዘላለም ነህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከቤትህ ርቀን መኖር ከቶ አንችልም
ከአንተ ተለይተን እርካታ አናገኝም
ከውሃ እንደወጣ ዓሣ እንሆናለን
ስለዚህ ጌታ ሆይ አንተን እንሻለን (፪x)
አዝማች · Chorus
አንተ ታዋጣናለህ ጌታ ታዋጣናለህ
አንተ ታዛልቃለህ ኢየሱስ የዘላለም ነህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ