በነገርህ ፍጹም
Benegereh Fetsum
2004 · ትራክ 7 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በነገርህ ፍፁም ነህ እግዚአብሔር (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እንደሰው አይደለህ ሚዛንህ አባይ
በቅን ትፈርዳለህ ተቀምጠህ በላይ (፪x)
ሸንጋይ አንደበትም የለብህም
ሐጥኡን ጻድቅ ነህ አንተ አትለውም (፪x)
ለሁሉ እንደሰራው ትከፍለዋለህ
በደል አትፈጽምም አድሎም የለብህም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የሰው ይግባኝ ሰሚ ፍርድህ ትክክል ነው
አምላኬ እንዳንተ ቅን የሆነ ማነው
ማስተዋልህም አይመረመር
ሁሌ ጽድቅ ነው ፍርድህ እግዚአብሔር
ዓይንህ እንዳየ ጆሮህ እንደሰማ መች ትፈርዳለህ
ለአሕዛብ እንኳን በቅድስና ትበይናለህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ