ሰበብ ፈላልጌ
Sebeb Felalegie
2004 · ትራክ 6 · አማርኛ
እዘምራለሁ እዘምራለሁ እዘምራለሁ
ለእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር
በብዙ ምስጋና ፊቱ እቆማለሁ (፬x)
ክበር ክበር ክበርልኝ
ንገሥ ንገሥ ንገሥልኝ (፪x)
አይጠፋም ከህሊናዬ ያረክልኝ
በልቤ ጽላት ተጽፏል የዋልክልኝ
አይጠፋም ከህሊናዬ ያረክልኝ
በልቤ ክታብ ይኖራል የዋልክልኝ
ተጐትጉቼ አይደለም ጌታን የማመልከው
ስለተደረገልኝ ደግሞም ስለሚገባው ነው
ልቤን ፈነቃቅሎ ነድሎ የሚወጣ አለኝ ብዙ ምስጋና
የፍቅር እጅ መንሻ ቢሆንልኝ እስቲ ልሰዋለት ደስ እያለኝ
ክበር ክበር ክበርልኝ
ንገሥ ንገሥ ንገሥልኝ (፪x)
አንድ ጊዜ ስለሁሌ ራስ ህን ሰጠኸኝ
የቀራንዮ ወዳጅ እኔን የወደድከኝ
ዛሬም በአብ ቀኝ ሆነህ የምትማልድልኝ
ከሞት ከሃጥያት እስራት ነፃ ያወጣኸኝ
ሰበብ ፈላልጌ ምክንያት ፈላልጌ ላሞጋግስህ (፪x)
አልጣጣም አለኝ ምስጋናዬ
ካረግክልኝ ጋራ በኑሮዬ (፪x)
የእለታት ዑደት በሚለዋውጡት እረፍት
አሳርፈኸኛል ለኔስ ሆኗል ሁሌ ሰንበት
ዓለም የማታውቀው የማትሰጠውን
ሰጥተኸኛል ሰላም አይምሮ የሚያልፈውን
ሰበብ ፈላልጌ ምክንያት ፈላልጌ ላሞጋግስህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ