የምስራች
Yemeserach
2004 · ትራክ 3 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የምስራች የምትነግሪ ፅዮን ሆይ
ከፍ ወዳለው ተራራ ውጪ
አትቆጥቢ ድምጽሽንም አሰሚ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እነሆ አምላክሽ ሊያከብርስ ወዷል
የክብርን ካባ ባንቺ ላይ ጥሏል
ነገሥታት ሁሉ ላንቺ ይሰግዳሉ
አሕዛብ ፊትሽ ይዋረዳሉ
ሙላት አድርጐ ልጁን ሰጥቶሻል
ስለዚህ ፅዮን ምን ያሰጋሻል
ቁጥር 2 · Verse 2
በተራሮች ላይ በድል ቁሚና
ምድሪቱን ሙይ ገዢ ሁኝና
መቅረዞችሽም ዘይትን ይሙሉ
በክብርም ላይ ክብር ይጨምሩ
ለሰጠሽ ተስፋ ፍፃሜ አለና
አዝማች · Chorus
ተነሺ ፅዮን አብሪ እንደገና
ፍጥረት ተጨንቆ በብዙ ውጥረት
ይጠባበቃል የአንቺን መገለጥ
ገዢ ሁኚና ከሁሉ የበላይ
ፅዮን ተነሺ በምድሪቱ ላይ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ