ወደደኝ
Wededegn
2004 · ትራክ 5 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ወደደኝ እኔም ወደድኩት ኮኮቤ ተጋጠመልኝ
በኢየሱስ መመረጤ ለእኔስ መልካም ሆነልኝ
ገመዴ ባማረ ስፍራ ወደቀችልኝ አሃሃ
እርስቴ በእርሱ በአምላኬ ተዋበችልኝ አሃሃ
ኧረ እንዴት እድለኛ ነኝ
ኧረ እንዴት እድለኛ ነኝ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ልጅ ተብዬ ተጠራሁኝ በቃ ተሻረ ባርነቴ
ስሜ በሰማይ ተጻፈ ከቅዱሳን ጋር ሆነ ቤቴ
እርስቴ ሆነልኝ በላይ
በሌለበት ተቀናቃኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ወደደኝ እኔም ወደድኩት ኮኮቤ ተጋጠመልኝ
በኢየሱስ መመረጤ ለእኔስ መልካም ሆነልኝ
ገመዴ ባማረ ስፍራ ወደቀችልኝ አሃሃ
እርስቴ በእርሱ በአምላኬ ተዋበችልኝ አሃሃ
ኧረ እንዴት እድለኛ ነኝ
ኧረ እንዴት እድለኛ ነኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አያሰጋኝም ከእንግዲህ የመጨረሻዬ ነገር
ለእኔስ ወድቆልኛል እጣ ከኢየሱሴ ጋራ መክበር
ቤት ተሰርቶልኝ በስሜ
ተውቧል የኔስ ፍፃሜ (፪x)
አዝማች · Chorus
ወደደኝ እኔም ወደድኩት ኮኮቤ ተጋጠመልኝ
በኢየሱስ መመረጤ ለእኔስ መልካም ሆነልኝ
ገመዴ ባማረ ስፍራ ወደቀችልኝ አሃሃ
እርስቴ በእርሱ በአምላኬ ተዋበችልኝ አሃሃ
ኧረ እንዴት እድለኛ ነኝ
ኧረ እንዴት እድለኛ ነኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
መላእክት ጉባዔ ጋር በዝማሬ ታድሜያለሁ
ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት ላሸበሽብ ተጠርቻለሁ
ክብር ለኢየሱስ እያልኩኝ ዘላለም አከብረዋለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ወደደኝ እኔም ወደድኩት ኮኮቤ ተጋጠመልኝ
በኢየሱስ መመረጤ ለእኔስ መልካም ሆነልኝ
ገመዴ ባማረ ስፍራ ወደቀችልኝ አሃሃ
እርስቴ በእርሱ በአምላኬ ተዋበችልኝ አሃሃ
ኧረ እንዴት እድለኛ ነኝ
ኧረ እንዴት እድለኛ ነኝ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እድለኛ ነኝ እድለኛ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ