Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እኔስ በምህረትህ ብዛት

Enies Bemhereteh Bezat

2004 · ትራክ 9 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እኔስ በምህረትህ ብዛት ወደ ቤትህ ገብቻለሁ

ከመድሃኒት ምንጮች በደስታ ውኃን እቀዳለሁ

ለዘላለም በቤትህ እኖራለሁ (፫x)

ምህረትህ ብዙ ብዙ ነው

ጌታዬ ለኔ ያረከው

የለኝም ቃላት መግለጫ

ባወራው ከቁጥር በዛ (፪x)

ሐጢዓቴን ነግረውህ እንድትፈርድብኝ

ከሳሾቼ አምጥተው ፊትህ ሲያቆሙኝ

ጥበብን ተናግረህ ነፃ አውጥተኸኛል

የነፍሴ መድሃኒት ሞገስ ሆነኸኛል

ውለታህ ከእምሮዬ በለጠብኝ ጌታዬ (፪x)

ስጦታህ ከእምሮዬ በለጠብኝ ጌታዬ (፪x)

እንባዬን ከዓይኔ አብሰሃል

ሃዘኔን በደስታ ለውጠሃል

እግዚአብሔር አንተ ምን ይሳንሃል

ምስኪኑን አንስተህ አክብረሃል (፪x)

ውለታህ ከእምሮዬ በለጠብኝ ጌታዬ (፪x)

ስጦታህ ከእምሮዬ በለጠብኝ ጌታዬ (፪x)

በአንተ ያላገኘሁት ምን አለ

ፅዋዬ ሞላ ተትረፈረፈ

አላጐደልኩም ጌታዬ

ከፍ ያርግህ ሁሌ ምስጋናዬ

ከፍ ያርግህ ሁሌ ምስጋናዬ (፪x)

ውለታህ ከእምሮዬ በለጠብኝ ጌታዬ (፪x)

ስጦታህ ከእምሮዬ በለጠብኝ ጌታዬ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ