ታማኝ ነው እግዚአብሔር
Tamagn New Egziabhier
2004 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አፌን በሳቅ ሞላ ምላሴን በእልልታ
ጠላቴ ማቅ ለበሰ አከበረኝ ጌታ
አንገት አያስደፋ አምላኬ አያሳፍር
በፊቱ የሆንኩለት ታማኝ ነው እግዚአብሔር
አዝማች · Chorus
ታማኝ ታማኝ ነው እግዚአብሔር
ታማኝ ታማኝ ነው አምላኬ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የኔን ላብ ለሌላ ከቶ አያሳልፍም
ውለታ ከፋይ ነው ወጨትን አይሰብርም
ሲደርስ በሰዓቱ ፈጥኖ ከተፍ ይላል
አምላኬ እግዚአብሔር እንዳለው ያደርጋል
አዝማች · Chorus
ታማኝ ታማኝ ነው እግዚአብሔር
ታማኝ ታማኝ ነው አምላኬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ፍርዱ አይዛባ ጻድቅ በመንገዱ
ልጆቹን ያስባል ጌታ እንደፈቃዱ
ቢያጠፋ ቢያለማ ትክክለኛ ነው
አምላኬን ተሳሳትክ የሚለው ሰው ማን ነው
አዝማች · Chorus
ታማኝ ታማኝ ነው እግዚአብሔር
ታማኝ ታማኝ ነው አምላኬ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
በንጉሥ ቀለበት ማህተም ቢታተም
የአምላኬ ጉልበት ከመስራት አይዝልም
አዋጅን በአዋጅ ጌታ ይሽረዋል
ያከበሩትንም ጌታ ማክበር ያውቃል
አዝማች · Chorus
ታማኝ ታማኝ ነው እግዚአብሔር
ታማኝ ታማኝ ነው አምላኬ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
አይቸኩል አይዘገይ አያልፍ ከስዓቱ
ሁሌ በመታመን እንሁን በፊቱ
ቀንዳችንን ከፍ ከፍ በጊዜው ያደርጋል
ሐናን እንዳሰበ እኛንም ያስባል
አዝማች · Chorus
ታማኝ ታማኝ ነው እግዚአብሔር
ታማኝ ታማኝ ነው አምላኬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ