አንተ አትለወጥም
Ante Atelewetem
2004 · ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዓለም ሳይፈጠር በነበረው ክብርህ
ዛሬም ሳትለወጥ አለህ በዙፋንህ
የዘላለም አምላክ የዘላለም ጌታ
አንተ ያው አንተ ነህ መቼም አትረታ
አዝማች · Chorus
አንተ አትለወጥም አንተ አትለወጥም
ጌታ አትለወጥም ጌታ አትለወጥም (፪x)
ዛሬም ያው ነህ እንደትላንትናው ነህ
የእኔ ጌታ መቼ ትለወጣለህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በኛ ላይ አላማህ ዘላለም ፍቅር ነው
ጊዜና ሁኔታ ዘመን የማይሽረው
እግዚአብሔር ወደደን እስከመጨረሻው
ፍቅሩ አያሰጋ ወረትም አያውቀው (፪x)
አዝማች · Chorus
አንተ አትለወጥም አንተ አትለወጥም
ጌታ አትለወጥም ጌታ አትለወጥም (፪x)
ዛሬም ያው ነህ እንደትላንትናው ነህ
የእኔ ጌታ መቼ ትለወጣለህ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጥንት ከአባቶቻችን ጋር እንደነበርህ
እንደ ኃያል እንደ ጨካኝ አብረህ እንደወጣህ
ዛሬም ከእኛ ጋራ አብረህ ትወጣለህ
በሰልፉ ሜዳ ላይ ድል ትሰጠናለህ (፪x)
አዝማች · Chorus
አንተ አትለወጥም አንተ አትለወጥም
ጌታ አትለወጥም ጌታ አትለወጥም (፪x)
ዛሬም ያው ነህ እንደትላንትናው ነህ
የእኔ ጌታ መቼ ትለወጣለህ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እስከ ዓለም ፍፃሜ ከእናንተ ጋር ነኝ
እኔ አልለወጥም ዘመን አይሽረኝ
ብለህ እንደተናገርክ እግዚአብሔር በቃልህ
እኛ ምስክር ነን አንተም አልተለወጥክ (፭x)
አዝማች · Chorus
አንተ አትለወጥም አንተ አትለወጥም
ጌታ አትለወጥም ጌታ አትለወጥም (፪x)
ዛሬም ያው ነህ እንደትላንትናው ነህ
የእኔ ጌታ መቼ ትለወጣለህ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
መቼ ትለወጣለህ (፪x)
እንደትላንትናው ነህ (፪x)
መቼ ትለወጣለህ (፪x)
እንደትላንትናው ነህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ