Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አከብርሃለሁ

Akebrehalehu

2013 · ትራክ 5 · 6:02 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከብዙ ውሆች ድምጽህ ይበልጣል

አንዴ ተናግረህ ልቤ ተጽናንቶአል

ነፍሴ ተጠማች አንተን ለማየት

ገና በቅምሻ ኦሆ እጅዋን ሰጣለች

አከብርሃለሁ አከብርሃለሁ

አንተ የእኔ ነህ ተመርጫለሁ

አመልክሃለሁ ኣመልክሃለሁ

አንተ የእኔ ነህ ተመርጫለሁ

ላውራ ልናገር የአንተን ሥራ

ህያው ሆኛለሁ ከአንተ ጋራ

አይኔ ተጋርዶ እንዳላስተውል

መዳን ከአንት ኦሆ ለኔ ሆነልኝ

አከብርሃለሁ አከብርሃለሁ

አንተ የእኔ ነህ ተመርጫለሁ

አመልክሃለሁ ኣመልክሃለሁ

አንተ የእኔ ነህ ተመርጫለሁ

ያስከተተኝ ኦሆሆ ሰራዊት (ትውልድ) ነኝ የጌታዬ (፪x)

ገና እኖራለሁ አንተን ሳከብር

አስታጥቀኸናል ሕያው ቃልህን

እኔን ለይተህ በአንተ ስቀደስ

ተረድቻለሁ በመልካሙ እጅህ

አከብርሃለሁ አከብርሃለሁ

አንተ የእኔ ነህ ተመርጫለሁ

አመልክሃለሁ ኣመልክሃለሁ

አንተ የእኔ ነህ ተመርጫለሁ

ላልመለስ...

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ