በለስ ባታፈራ
Beles Batafera
2013 · ትራክ 2 · 6:50 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምንም እንኩዋን በለስ ባታፈራ
በወይን ሀረግ ፍሬ ባይገኝ
በወይራ ስራ ቢጎድል
እርሾች መብል ባይሰጡ
ላሞች በጋጣ ባይገኙም
በጐች ከበረት ቢጠፉም
አዝማች · Chorus
በአንተ ደስ ይለኛል (፮x)
በመጠባበቂያዬ እጠብቃለሁ
አንተን ተስፋዬን አገኝሃለሁ (፮x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ምንም እንኩዋን በለስ ባታፈራ
በወይን ሀረግ ፍሬ ባይገኝ
በወይራ ስራ ቢጎድል
እርሾች መብል ባይሰጡ
ላሞች በጋጣ ባይገኙም
በጐች ከበረት ቢጠፉም
አዝማች · Chorus
ብዙዎች ለማየት የተመኙትን
ዓይኖች አይተዋል ተስፋ የክብሩን (፪x)
ብዙዎች ለማየት የተመኙትን
ዓይኖች አይተዋል ተስፋ የክብሩን (፭x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታ እግዚኣብሔር ሃይሌ ነው
እግሮቼን እንደ ዋላ የሚያጠነክረው
በከፍታ የሚያስኬደው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ