Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በእሳት የሚመልስ

Besat Yemimeles

2013 · ትራክ 6 · 7:28 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ያለውን ይፈፅማል

ታማኝ ነው አይተነዋል

በእሳት የሚመልስ

እርሱ ነው የእኔ ንጉሥ (፪x)

እርሱ ነው የተነሳው

እርሱ ነው ከፍ ከፍ ያለው

የኢየሱስ ነው (፪x)

ነጻ ብሎ ኢየሱስ ፈቶኛል

የከበደኝን ቀንበሬን ሰብሮአል

ሁሉ አዲስ ሆኖ ተፈጥሬአለሁ

በፀጋው ብቻ ኦሆ በእርሱ እመካለሁ

ተደርጐልኛል ኦሆሆ

መቼ በሥራ ነው ኦሆ

በፀጋው ብቻ ኦሆሆ

በእርሱ እመካለሁ (፭x)

ይጠብቁኝ ዘንድ መላእክቱን አዟል

በእሳት ቀጥሮ ያራምደኛል

ብርቱ ተዋጊ ሥሙም እግዚኣብሔር

እረኛዬ ነው ኦሆሆ መቼም አይተኛም

ብርቱ ተዋጊ ኦሆ ኦሆ

ሥሙም እግዚኣብሔር

እረኛዬ ነው ኦሆ ኦሆ

መቼም አይተኛም

ተናግሮ...

ባጠገቤ ሺህ በቀኝ አስር ሺህ

ጠላቴ ወድቆ በዓይኔ ብቻ አየሁ

ከእኔ ጋር ያለው ብርቱ ኃይል ነው

ከኃይል ወደ ኃይል ኦሆ ኦሆ እሻገራለሁ

ባጠገቤ ሺህ ኦሆ ኦሆ

በቀኝ አስር ሺህ አሄ

ከኃይል ወደ ኃይል ኦሆ

እሻገራለሁ እራመዳለሁ (፬x)

ተናግሮ...

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ