ዕልል ብዬ
Elel Beyie
2013 · ትራክ 1 · 5:54 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ዕልል እልል ብዬ (፪x)
ላከብርህ ነው ተራዬ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ፈርዖንም ቢፎክር የመረጥከውን ሊያስገብር
ብዙ ጣረ ደከመ የአንተን ሀሳብ ሊቀይር
ትእዛዝ ወጥቶአል ከሰማይ አታቆመው በአንተ ኃይል
ላትነሳ ወድቀሃል ህዝቡን ፈቶኣል አዶናይ
የተገለጠውን ብርሃን
ሕይወት ሆኖ አየሁት በዓይኔ
መኖር መርጫለሁ ዛሬ
አቻ አልተገኘለት ክብሬ
ቁጥር 2 · Verse 2
ኦሆ ክብሬ (፪x)
አትሻር አትለወጥ የጸና ነው ዙፋንህ
አታረጅ አትደክም ትኖራለህ በክብር
ከስም በላይ ስም አለህ ከአብ ዘንድ የተሰጠህ
ጉልበት ሁሉ ይንበርከክ ከፍ ላለው ይስገድ
አዝማች · Chorus
ዕልል እልል ብዬ (፪x)
ላከብርህ ነው ተራዬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በኃይል አይደል በብርታት
መች በራስ ነው በጥረት
በነጻ ነው ቸርነት
በእርሱ ሆነ በመንፈስ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የተገለጠውን ብርሃን
ሕይወት ሆኖ አየሁት በዓይኔ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ