ባሕር ከፍለሃል
Baher Keflehal
2013 · ትራክ 8 · 5:14 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጌታ አንተን ስለምን
ጌታ አንተን ስጠራ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጌታ ደጁን ሳንኳኳ
ኦ ሄይ (፪x)
አይቼ የማላውቀው ጆሮዬም ያልሰማው
አፈለቅህ ለእኔ ከአለቱ ውሃ
ባሕር ከፍለሃል ማዕበሉን ገስጸህ
እኔን አሻገርክ በደረቅ መሬት
ሰማያዊ ነው የተሰጠኝም ዜግነት
እርስቱ አድርጎ የሚገዛበት
ታድገህኛል የበጉን ደም ለእኔ አፍሰህ
ፍርዴን አስቀረኸው መስዋእት ሆነህ
ትጥቅና ምግቤ ተለይቶ በግብጽ ማታ
አረማመዴ ታዟል ከጌታ
አዝማች · Chorus
ጌታ አንተን ስለምን
ጌታ አንተን ስጠራ
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታ ደጁን ሳንኯኯ
ኦ ሄይ (፪x)
ገበሬው አብ ነው ነኝ እኔ የአምላኬ እርሻ
የማይጠፋው ዘር የማፈራበት
ልብሴ አያረጅም ጫማዬም ከቶ አያልቅም
በትንሳኤው ሃይል ሕይወቴ ጸንቷል
አዝማች · Chorus
ጌታ አንተን ስለምን
ጌታ አንተን ስጠራ
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታ ደጁን ሳንኯኯ
ኦ ሄይ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ