ይህች ቀን
Yehech Qen
2013 · ትራክ 10 · 6:38 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ይህች ቀን ለእኔ ነች ጌታ የሰራት
ከሕግ ባርነት ነጻ ወጣሁባት (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አዲስን ምዕራፍ በእርሱ አየሁባት (፪x)
ተደላድዬ በእርሱ እኖራለሁ
ሌሎች የዘሩትን እኔ አጭዳለሁ
በተጠናቀቀው በእሱ እኖራለሁ
አዎ (፬x)
ፊደል ሕይወት አይሆን መንፈስ ካልመጣልኝ
በፀጋ ላይ ፀጋ ተትረፈረፈልኝ
መውደዱን ገለጸ ስለ እኔ ሞቶልኝ
መች ቃሉን ያጥፍና ተናግሮአል ጌታዬ
ኦሆ ለእኔ (፮x)
አዝማች · Chorus
ይህች ቀን ለእኔ ነች ጌታ የሰራት
ከሕግ ባርነት ነጻ ወጣሁባት (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታ አሳርፎኛል ስራዬን ሰርቶልኝ
መቅበዝበዜ አበቃ ምንም አልጨምርም
አንድም አላስቀረም ሁሉን ፈጽሞልኝ
ከክርስቶስ ጋራ ወራሽ አደረገኝ
አደረገኝ (፪x)
ኦሆ እኔን ኦሆሆ እኔን (፪x)
አዝማች · Chorus
ይህች ቀን ለእኔ ነች ጌታ የሰራት
ከሕግ ባርነት ነጻ ወጣሁባት (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጽድቄ ከእግዚኣብሔር ነው በነጻ ተሰጥቶኝ
ሚኮንነኝ ማነው እርሱ ከወደደኝ
ኃጢአት ተወገደ በጌታዬ በኢየሱስ
ሞት መውጊያው ተቀማ በሕይወት እንድነግስ
እንድነግስ
ኦሆ እንድነግስ ኦሆሆ እንድነግስ (፪x)
አዝማች · Chorus
ይህች ቀን ለእኔ ነች ጌታ የሰራት
ከሕግ ባርነት ነጻ ወጣሁባት (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ