Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ስላንተ

Selante

2013 · ትራክ 7 · 6:36 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ቃልህን ሰምቼ ሥራህን አይቼ

አይኔ በርቶልኛል አንተ ነህ ጌታዬ

እዚህም እዚያም አልልም ለቅቄህ አልሄድም

በጥበቃህ ሥር ነኝ አልሻም ሌላውን (፫x)

ኦሆ

ስላንተ ያወራሉ ሰው ሲናገር ስለሰሙ

የሰው ስርዓት ወግ ልማዱ ሕይወት የለሽ አምልኮውን

ኃይል ብርታቱን የከዳውን መች ሊገባኝ እርሱን ላየው

በእውነት ልስገድ ለሚገባው

ወደር መሳይ ለእኔ የለው

በእውነት ላክብር ስለምወደው

ኦሆ

ለደካማው ብርታት ለዛለውም ጉልበት

ማለምለምን ሚወድ ድንቅ መካር ሀያል ነው

የኢየሱስ ከኔ ጋር ነው ማንን እፈራለሁ

የሚያቆመኝ የለም ከፍ ብዬ እሄዳለሁ

እንደ ንስር እወጣለሁ

ከፍ ብዬ እሄዳለሁ

ኦሆ

ስላንተ ያወራሉ ሰው ሲናገር ስለሰሙ

የሰው ስርዓት ወግ ልማዱ ሕይወት የለሽ አምልኮውን

ኃይል ብርታቱን የከዳውን መች ሊገባኝ እርሱን ላየው

በእውነት ልስገድ ለሚገባው

ወደር መሳይ ለእኔ የለው

በእውነት ላክብር ስለምወደው

ያማረ ዝማሬ ቅኔዬም ለእርሱ ነው

ሁሉ ከእርሱ በእርሱ ለእርሱ ነው የምሰጠው

በገና ልደርድር መሰንቆዬን ላንሳ

የከንፈሬን ፍሬ ዜማዬን ላሰማ

ምሥጋና ላሰማ ዜማዬን ላሰማ

ስላንተ ያወራሉ ሰው ሲናገር ስለሰሙ

የሰው ስርዓት ወግ ልማዱ ሕይወት የለሽ አምልኮውን

ኃይል ብርታቱን የከዳውን መች ሊገባኝ እርሱን ላየው

በእውነት ልስገድ ለሚገባው

ወደር መሳይ ለእኔ የለው

በእውነት ላክብር ስለምወደው

ፍሬ የለሽ ከንቱ ወሬ መች ኣውቃለሁ

የአንተን ቃል በንፁህ ልብ እኔ አምናለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ