Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፍቅርህ

Feqreh

2013 · ትራክ 4 · 6:59 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ፍቅርህ ከሞት ይልቅ ብርቱ ነው

ሕይወቴን እንደ መልሕቅ ያጸናው

መልካሙን ተስፋ ያስያዘው

በልቤ የሞላው እርሱ ነው (፪x)

ሳልወድህ ገና አንተ ወደድከኝ

የሚረባኝን አንተ አስተማርከኝ

ሳላውቅህ ገና አንተ አወቅከኝ

ከአዳኝ ወጥመድ ነጥቀህ አስጣልከኝ

እንዲህ ላረከው ምን አስቀራለሁ

በምላሽ ይኸው እዘምራለሁ (፫x)

ፍቅርህ ከሞት ይልቅ ብርቱ ነው

ሕይወቴን እንደ መልሕቅ ያጸናው

መልካሙን ተስፋ ያስያዘው

በልቤ የሞላው እርሱ ነው (፪x)

በልቤ ፈሶ የአንተ ፍቅር

ጠራርጐ ያወጣል የክፋትን ዘር

ግንዱ ኢየሱስ ነው የኔ መሰረት

የሕይወት ራስ የተፈጠርኩበት

ሁሉ ከርሱ ነው የሆነው ሕይወት

ትምክት የለኝም የምመካበት (፫x)

ፍቅርህ ገዢ ነው አያውቅም ክፋት

ፍጥረትን ማርኮ ያንበረከከ

ሕልውናህ ነው የአንተ ባህሪህ

ፀንቶ ሚቀጥል ከሁሉ ሚበልጥ

ሕግን ፈጽሞ የጠቀለለው

ፍቅርህ እኮ ነው በደል የማይቆጥረው (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ