ተብሎ ያላለቀ
Tebelo Yalaleqe
2013 · ትራክ 9 · 4:59 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ተብሎ ያላለቀ ተነግሮ ያልተሰማ
ለኔ ያለው የተሻለ አይን ያላየው የከበረ (፪x)
ተብሎ ያላለቀ ተነግሮ ያልተሰማ
ለኔ ያለው የተሻለ አይን ያላየው የከበረ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ውዴ ያንተን ቃል ሰምቻለሁ
የናፈቅኩትን አግኝቼዋለሁ
ሃሳቤን የእኔን አስወግጄአለሁ
አንተ የእኔ ነህ አመልክሃለሁ (፫x)
አዝማች · Chorus
ተብሎ ያላለቀ ተነግሮ ያልተሰማ
ለኔ ያለው የተሻለ አይን ያላየው የከበረ (፪x)
ተብሎ ያላለቀ ተነግሮ ያልተሰማ
ለኔ ያለው የተሻለ አይን ያላየው የከበረ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አንተን ለሚወዱ እንደ ሃሳብህ ለተጠሩ
ነገር ሁሉ ለበጎ ነው
እንዳሰብከው እንዳወቅከው
መታመን በአንተ ለእኔ ማትረፍ ነው
ቀድሞ ያየውን ነው የምኖረው
ስጋት ሳይገባኝ እራመዳለሁ
መልካም መልካም ነው ካንተ የሚፈልቀው
በቤትህ ሁሌ እዘምራለሁ
መልካም መልካም ነው ካንተ የሚፈልቀው
አዝማች · Chorus
ተብሎ ያላለቀ ተነግሮ ያልተሰማ
ለኔ ያለው የተሻለ አይን ያላየው የከበረ (፪x)
ተብሎ ያላለቀ ተነግሮ ያልተሰማ
ለኔ ያለው የተሻለ አይን ያላየው የከበረ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ፍጻሜና ክብር የሞላበት ተስፋ
ነው ያቀረበልኝ ኢየሱስ የእኛ ጌታ
ያልከው ሆነ
ሃሳብህ ተፈጸመ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ