ገናና ነህ
Genana Neh
2013 · ትራክ 3 · 4:48 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ቅጥሬ መዳን ሆኖአል ጌታ
በሬ ምስጋና
ነገሥታት የክብርህን ጸዳል ያያሉ
አሕዛብ ለግርማህ ይሰግዳሉ
ብርሀን በርቶአልና በድቅድቁ (፫x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ይገርማል የአንተ ጥበብ
ሰማይን ዘርግተሃል
በቃልህ ሁሉ ፀንቶአል
በቃልህ ሁሉ ፀንቶአል (፪x)
ብርቱ ነህ አንተ ብቻ ገናና ነህ ገናና (፪x)
ከፍ ያልከው ለዘላለም ገናና ነህ ገናና (፪x)
አትሻር አትለወጥ ገናና ነህ ገናና (፪x)
ከጥንትም ህያው ነበርክ ገናና ነህ ገናና (፪x)
አዝማች · Chorus
ቅጥሬ መዳን ሆኖአል ጌታ
በሬ ምስጋና
ነገሥታት የክብርህን ጸዳል ያያሉ
አሕዛብ ለግርማህ ይሰግዳሉ
ብርሀን በርቶአልና በድቅድቁ (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከአፍህ የወጣው ቃል ገናና ነህ ገናና (፪x)
ያሻህን ይፈጽማል ገናና ነህ ገናና (፪x)
በከንቱ አይመለስ ገናና ነህ ገናና (፪x)
አይተናል ሲያረሰርስ ገናና ነህ ገናና (፪x)
አዝማች · Chorus
ቅጥሬ መዳን ሆኖአል ጌታ
በሬ ምስጋና
ነገሥታት የክብርህን ጸዳል ያያሉ
አሕዛብ ለግርማህ ይሰግዳሉ
ብርሀን በርቶአልና በድቅድቁ (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አሀዱ መጀመሪያ ገናና ነህ ገናና (፪x)
ተፈጥሮአል ባንተ ብቻ ገናና ነህ ገናና (፪x)
አይኖርም ካንተ ሌላ ገናና ነህ ገናና (፪x)
ኦሜጋ መደምደሚያ ገናና ነህ ገናና (፪x)
በኃይሉ ብርታት የገነነ
ከፍ ከፍ ከፍ ያለ
ከፍ ከፍ ከፍ ያለ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ