Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አለ ገና

Ale Gena

2011 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ያኔ የነገርከኝ በምድረ በዳ ላይ

ሚታይ በሌለበት ስትገባልኝ ኪዳን

ወደ በረከት ጠርተህ ያወራኀኝ

ይሆናል ጠብቀው ታየዋለህ ያልከኝ

አየሁት ጀምሯል በሕይወቴ (፪x)

መፈጸም ጀምሯል በሕይወቴ (፪x)

አየሁት ጀምሯል በሕይወቴ (፪x)

መፈጸም ጀምሯል በሕይወቴ (፪x)

የነገርከኝ አለ (አለ ገና ገና)

ማንም ሳይኖር ከጐኔ (አለ ገና ገና)

ምድረ በዳ ላይ ሆነን (አለ ገና ገና)

ዘርህ በዝቷል ስትለኝ (አለ ገና ገና)

የነገርከኝ አለ (አለ ገና ገና)

ማንም ሳይኖር ከጐኔ (አለ ገና ገና)

ምድረ በዳ ላይ ሆነን (አለ ገና ገና)

ትውልድ አለ ስትለኝ (አለ ገና ገና)

(እንደገና) ጌታ መርቆ

(እንደገና) የሸኘው ሰው

(እንደገና) መሃል መንገድ ላይ ማነው ሚያስቀረው

(እንደገና) ነገር ጀምሯል

(እንደገና) የምርቃቱ

(እንደገና) እንዳሸዋ ነው የበዛው ባርኮቱ (፱x)

የሰማነው አለ (አለ ገና ገና)

ለአባቶች ከነገርከው (አለ ገና ገና)

በኢትዮጵያ ምድር ላይ (አለ ገና ገና)

ኢየሱስን ልታገነው (አለ ገና ገና) (፪x)

(እንደገና) ከዳር እስከ ዳር

(እንደገና) በወንጌል እሳት

(እንደገና) ገና እናያለን

(እንደገና) ምድሪቱ ለኩሰው

(እንደገና) ከቶ የማይጠፋ

(እንደገና) ሰው ያልጀመረው

(እንደገና) የማይቆም ክብር ጌታ ሊያሳየን ነው (፱x)

ጌታ ሊያሳየን ነው የማያቆም ክብር

ጌታ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ