የመልካምነትህ
Yemelkameneteh
2011 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሁልጊዜ እኔ የሚገርመኝ
ራሴን ሳየው ስቃኘው ኋላዬን
በሄድኩበት በሕይወት መንገድ
ያሳረፍከኝ አለ ምልክት
ጌታ ኢየሱስ የመልካምነትህ
አዝማች · Chorus
አቤት የመልካምነትህ
አቤት የአባትነትህ
አቤት እኔን አኑረሃል
አቤት እንዲህ አሳድገህ (፪x)
ዓይኖቹን አንስቶ አንተን የጠበቀ (፫x)
መች እንዲሁ ይቀራል ትጐበኘዋለህ (፫x)
ተሰብረህ ማትወጋ ለተደገፉብህ (፫x)
አቅም ትሆናለህ በእውነት ለሚጠሩህ (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ስለአንተ ላወራ እኔም ልናገር
እድሉን አገኘሁ ከአረክላቸው ጋር
በአንተ ነው ያየሁት ብሩህ ቀን ለራሴ
ወደ ደካማው ሰው ስትመጣ ኢየሱሴ (፪x)
እንዴት ነው ምትወደኝ እኔን
ምንም ሳልሰራልህ ለምን
ምን አይነት ፍቅር ነው ያለህ
እኔን የወደድክበት (፪x)
እኔማ (፰x) እኔማ ያየሁት ኢሄን ነው
እኔማ ኢየሱስ በዘመኔ
እኔማ መልካምነትህን ነው
እኔማ ማወራው ከልቤ
አዝማች · Chorus
አቤት የመልካምነትህ
አቤት የአባትነትህ
አቤት እኔን አኑረሃል
አቤት እንዲህ አሳድገህ (፪x)
ዓይኖቹን አንስቶ አንተን የጠበቀ (፫x)
መች እንዲሁ ይቀራል ትጐበኘዋለህ (፫x)
ተሰብረህ ማትወጋ ለተደገፉብህ (፫x)
አቅም ትሆናለህ በእውነት ለሚጠሩህ (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከፊትህ ጋር ደስታ አጠገብከኝና
ዘመኔ ለምልሟል ብርሃንህ በራና
ሕይወቴን የገዛ የድንግዝግዝ ኑሮ
ላላየው አለፈ ሁሉ ተቀይሮ (፪x)
እንዴት ነው ምትወደኝ እኔን
ምንም ሳልሰራልህ ለምን
ምን ዐይነት ፍቅር ነው ያለህ
እኔን የወደድክበት (፪x)
እኔማ (፰x) እኔማ ያየሁት ኢሄን ነው
እኔማ ኢየሱስ በዘመኔ
እኔማ መልካምነትህን ነው
እኔማ ማወራው ከልቤ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ