ማዳኑ ከፍ ያለ ነው
Madanu Kef Yale New
2011 · ትራክ 11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ይወርሰኛል ብዬ የፈራሁት ነገር የቆመ በበር
አይሆንም አለ ጌታ ከሰማያት ቃል ወጣ ስለእኔ
ራራልኝ ውዴ (፪x)
ወጀብ አለ ከፊት አትፍራ አለኝ ጌታዬ
ተገልብጧል ነገሩ ቃል ወጥቷል ዛሬ ለእኔ
በመንገድ ሊያስቀረኝ ሊገታኝ የነበረ
ቀደምኩት አለኝ ጌታ ወጥመዱ ተሰበረ
ማነው ማዕበሉን የገሰጸው
ማነው ወጀቡን ጸጥ ያደረገው
ማነው ይሁን ሲል ሚሆንለት
ማነው የአፉ ቃል ሚጸናለት
አዝማች · Chorus
ጌታዬን ነው ጌታዬ ያየሁት በዘመኔ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ፈርቶት የሩቅ ዘመኔን ቢነሳ ያ ጠላቴ
ጉልበቴን ሊያደክመው ቢቆምም በመንገዴ
ይሄዳል የኔ ነገር በቃል ሚኖር አይቆምም
ሰባሪው ከፊት ወጥቷል ሰብሬ አልፋለሁ እኔ
ማነው መንገዴን ያስጀመረኝ
ማነው መንገዴን ሚያስጨርሰኝ
ማነው ከፊቴ የቀደመው
ማነው መንገዴን የከፈተው
አዝማች · Chorus
ጌታዬን ነው ጌታዬ ያየሁት በዘመኔ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ንጉሥ ወርዶ ከሰማይ አይቆምም ፊቱ ከልካይ
ይታደጋል ያድናል ደርሶ ከሞት ያወጣል
እኔም የእርሱ ልጅ ሆኜ ድኛለሁ ከጠላቴ
ጠላት ያሴረው ሴራ መና ሆነ ፉከራ
ማዳኑ ከፍ ያለ ነው
ኢየሱስ ከፍ ያለ ነው
ሲረዳኝ ከፍ ያለ ነው
ሲያወጣኝ ከፍ ያለ ነው
ጌታ ሲረዳኝ ጌታ ሲያወጣኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ