ይገርማል ኢየሱስ
Yegermal Eyesus
2011 · ትራክ 3 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኢየሱሴ ስል ልቤ ውስጥ የሚገባው ፍቅር
ኢየሱስዬ ስል ልቤ ውስጥ የሚገባው ፍቅር
ኧረ ማን ሊተካው ኧረ ማን (፰x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ሲጠሩህ ረዳት ሚሹ
ኢየሱስ እርዳን እያሉ
ሲያስቆምህ የእነርሱ ጩኀት
ሲያቅትህ ትቶ ለማለፍ
ያዳንካችው ሁሉ ኢየሱሴ
እግርህ ስር ሲደፉ ኢየሱሴ
አብረንህ እንኑር ኢየሱሴ
ብለው ቢለምኑ ኢየሱሴ
አንዳንዶች ሲያለቅሱ ኢየሱሴ
አንሄድም እያሉ ኢየሱሴ
የትም ያላዩትን ኢየሱሴ
ፍቅር ሲያገኙ ኢየሱሴ
ኢየሱስ (፮x)
ይገርማል ኢየሱስ ይገርማል (፱x)
አዝማች · Chorus
ኢየሱሴ ስል ልቤ ውስጥ የሚገባው ፍቅር
ኢየሱስዬ ስል ልቤ ውስጥ የሚገባው ፍቅር
ኧረ ማን ሊተካው ኧረ ማን (፰x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በመስቀል ስራህ አዳንከኝ
በሞትህ ልጅህ አደረከኝ
ቀየርከው ዘለዓለሜን
ኢየሱስ ሞቴን ሞተህ
ዘመኔን ያሰረ ኢየሱሴ
የሕይወቴን ችግር ኢየሱሴ
የዓለም ዕውቀት ጥበብ ኢየሱሴ
አይፈታውም ነበር ኢየሱሴ
በስብከት ሞኝነት ኢየሱሴ
አንተን እሺ ብዬ ኢየሱሴ
የሰማሁ ለታ ኢየሱሴ
ቀረ ያ ታሪኬ ኢየሱሴ
ኢየሱስ (፮x)
ይገርማል ኢየሱስ ይገርማል (፱x)
ኢየሱስ (፪x) ያዳንከኝ ኢየሱሴ
ዘመኔን የቀየርከው ሕይወቴን የለወጥከው ታሪኬን ያደስከው ኢየሱሴ
ያው ነው
የእኔ ፈዋሽ የእኔ አዳኝ ኢየሱሴ
የዘላለምን ክብር ያሰየኝ
ኢየሱስ /3/
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ