Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የፍቅርህ ባለ ዕዳ

Bale Eda Negn

2011 · ትራክ 5 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የደህንነቴ መደምደሚያ

የክብር ስሜ ነህ መጠሪያ

ማዕረጌ ሆነህ በሞትህ

እኔም ተባልኩኝ ልጅህ (፪x)

የሞትህ ፍሬ የድካምህ

በጣር የወለድከኝ ልጅህ

በመከራ አልፈህ ያገኘኀኝ

የዕንባህ ልጅህ ነኝ (፪x)

እኔ ባለ ዕዳ ነኝ እኔ

የፍቅርህ ባለ ዕዳ ውለታህ ያለብኝ

እንዴት እንዴት ብዬ ነው

መክፈል የምችለው የፍቅርህን ሸክም

መቼም የማልመልሰው

ልክፈል እንኳን ብዬ ብጀምር ማለዳ

ፍቅርህን እንዲያው ሰጥተኀኛል

ታዲያ አይደለሁም ወይ የፍቅርህ ባለ ዕዳ

መራመድ አይችሉም እግሮቼ

ኢየሱስ በፍቅርህ ተይዤ

እንዳልሄድ ከቶ ወደሌላ

አርገኝ የፍቅርህ እስረኛ

አርገኝ የፍቅርህ እስረኛ

እንዳልሄድ ከቶ ወደሌላ

ኢየሱስ በፍቅርህ ተይዤ

መራመድ አይችሉም እግሮቼ

ንግሥና መጣ በደምህ - እኔ ባለ ዕዳ ነኝ

ክነቱም መጣ በሞት - ኧረ እኔ ባለ ዕዳ ነኝ

ደህንነት ሆነ በጸጋ - እኔ ባለ ዕዳ ነኝ

ልጅ መባል ቢሆን በስራህ - እኔ ባለ ዕዳ ነኝ

እኔማ የፍቅርህ ባለ ዕዳ

የምህረትህ ባለ ዕዳ ነኝ

መራመድ አልችልም እግሬ

ተይዣለሁ እኔ

ነፍሱን ለወዳጁ ሚሰዋ

ይገኝ ይሆናል በመከራ

ኢየሱስ የአንተ ግን ሚገርመው

ለጠላትህ የሞትከው (፪x)

እድሜ ዘመኔን የሚገዛ

ልቤን የያዘ ውለታህ

የፍቅር ዕዳ አኖርክብኝ

ሳልወድህ ወደድከኝ (፪x)

መልክህና ውበትህ ጠፋ - እኔ ባለ ዕዳ ነኝ

በሰው ተንቀህ ተጠላህ - ኧረ እኔ ባለ ዕዳ ነኝ

ተፈወስኩኝ አንተ ቆስለህ - እኔ ባለ ዕዳ ነኝ

ደዌ ህመሜን ወሰድህ - ኧረ እኔ ባለ ዕዳ ነኝ

</poem>

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ