ከፊት ሁን ኢየሱሴ
Kefit Hun Eyesusie
2011 · ትራክ 7 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ናና ከፊት ሁን ኢየሱሴ
ክብሬ ነህ አትሆንም ከኋላዬ (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በሰው መሃል ድፍረቴ
በሰው መሃል ድምቀቴ
በሰው መሃል ሕይወቴ
በሰው መሃል ውበቴ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በማይጠቅም በማይረባ ነገር
ልለውጠው አልችልም የዘለዓለም ክብሬን
እርሱ ነው ከመሬት አንስቶ
ያሳመረው ሕይወቴን ሞገሱን አፍሶ
ዛሬ ላየኝ ሰው ጌታ እንደዚህ ሰርቶ
ማለት አልችልም እጄ አደረገችው
እኔ አሳያለሁ ኢየሱስ ነው ብዬ
አልደብቀውም ክብሬን ከኋላዬ
አዝማች · Chorus
በእርሱ እኮ ነው (በጌታ) ፣ ክብር ያየሁት (በጌታ)
ያንን ዘመን (በጌታ) ፣ የረሳሁት (በጌታ)
ሌላውን (በጌታ) ፣ ተቀየረ (በጌታ)
ክብሬ ገብቶ (በጌታ) ፣ ቤቴ አማረ (በጌታ)
ለክብሬ (አለኝ ዛሬ) ፣ ዝማሬ (አለኝ ዛሬ)
ምሥጋና (አለኝ ዛሬ) ፣ ለጌታ (አለኝ ዛሬ)
ኢሄው እልልታ (አለኝ ዛሬ) ፣ ኢሄው ምሥጋና (አለኝ ዛሬ)
ኢሄው ሙገሳ (አለኝ ዛሬ) ፣ ኢሄው ለጌታ (አለኝ ዛሬ) (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የክብር የሞገስ አክሊሌ
ኢየሱስ ሆኖ መጣልኝ ሊለውጥ ታሪኬን
አይችልም ልቤም መራቅ ከእርሱ
እንዴት ሊሆንለት ነው ዘንግቶት ሞገሱን
ሙሽራ ጌጧን ደግሞ ዝርግፍ ጌጧን
ትረሳለች ወይ ውብ ያደረጋትን
እርሷ ካልረሳች እኔ እንዴት ብዬ ነው
ውብ ያደረገኝን ኢየሱስን ምረሳው
አዝማች · Chorus
በእርሱ አይደል ወይ (በጌታ) ፣ ክብር ያየሁት (በጌታ)
ያንን ዘመን (በጌታ) ፣ የረሳሁት (በጌታ)
ሌላውን (በጌታ) ፣ ተቀየረ (በጌታ)
ክብሬ ገብቶ (በጌታ) ፣ ቤቴ አማረ (በጌታ)
ለክብሬ (አለኝ ዛሬ) ፣ ዝማሬ (አለኝ ዛሬ)
ምሥጋና (አለኝ ዛሬ) ፣ ለጌታ (አለኝ ዛሬ)
ኢሄው እልልታ (አለኝ ዛሬ) ፣ ኢሄው ምሥጋና (አለኝ ዛሬ)
ኢሄው ሙገሳ (አለኝ ዛሬ) ፣ ኢሄው ለጌታ (አለኝ ዛሬ) (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ልቤ እምቢ ይለኛል (ሌላ) ፣ አላይ ወደ ኋላ (ሌላ)
ዓለም አትናፍቀኝ (ሌላ) ፣ ኢየሱሴን ብቻ (ሌላ) (፪x)
አዝማች · Chorus
ለክብሬ (አለኝ ዛሬ) ፣ ዝማሬ (አለኝ ዛሬ)
ምሥጋና (አለኝ ዛሬ) ፣ ለጌታ (አለኝ ዛሬ)
ኢሄው እልልታ (አለኝ ዛሬ) ፣ ኢሄው ምሥጋና (አለኝ ዛሬ)
ኢሄው ሙገሳ (አለኝ ዛሬ) ፣ ኢሄው ለጌታ (አለኝ ዛሬ) (፪x)
አለኝ (አለኝ ዛሬ) ፣ እህህህ (አለኝ ዛሬ)
አለኝ (አለኝ ዛሬ) (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ