Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በድካሜ ማግስት

Bedekamie Magest

2011 · ትራክ 9 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በድካሜ ማግስት ፊትህን ልይ አልል

ግን ውስጤ ናፍቆሃል ምን ብዬ ልናገር

ፊትህ ተደፍቼ ማረኝ አልኩህና

ትቼዋለሁ አልከኝ ቀና እረከኝና (፪x)

አቤቱ (፫x) እንደአንተ የሚገባው የለም

እንደ አንተ የሚሰማኝ የለም

እንደ አንተ የሚወደኝ የለም

እንደ አንተ ሚራራልኝ የለም (፪x)

በደል ፈጽሜ ፈርቼ

መንገድ ስጀምር ልሸሽ

ድንገት ናፍቀኀኝ መጥቼ

ድፍረቴን ሲነሳኝ ድካሜ

በእጆችህ የያዝከው (የያዝከው)

ምህረቴ ለአንተ ነው ያልከው

መለስካት ሕይወቴን ወደ አንተ (ወደ አንተ)

አልችልም በቃኝ ያለ አንተ

ፊትህን ከሰወርክብኝ ደነግጣለሁ

ዝም ካልከኝ ወደ ሞት ጉድጓድ ምወርድ እመስላለሁ

ፈሪ ነኝ/እፈራለሁ ያለ ህልውናህ ውሎም ለማደር

በርትቼም ደክሜም ቢሆን ምርጫዬ እግርህ ስር (፪x)

በረሃ ላይ በጥም ለከሰለ

ፍቅርህን ተጠምቶ ለዛለ

አባት ከደጃፍ ቆመሃል

ልጅህን ለማየት ናፍቀሃል

ደፍሬ አይደለም ወይ ንቂ

ይሄውና እስከ ድካሜ

ያለ አንተ እንደማልችል አውቂ

ወጣሁኝ አባቴን ብዬ

ፊትህን ከሰወርክብኝ ደነግጣለሁ

ዝም ካልከኝ ወደ ሞት ጉድጓድ ምወርድ እመስላለሁ

ፈሪ ነኝ/እፈራለሁ ያለ ህልውናህ ውሎም ለማደር

በርትቼም ደክሜም ቢሆን ምርጫዬ እግርህ ስር (፪x)

አቤቱ (፫x) እንደአንተ የሚገባው የለም

እንደ አንተ የሚሰማኝ የለም

እንደ አንተ የሚወደኝ የለም

እንደ አንተ ሚራራልኝ የለም

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ