Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፍቅርህ በልቤ

Feqreh Belebie

2011 · ትራክ 8 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጨምሮ ፍቅርህ በልቤ ሲገባኝ የመወደዴ

ተራዬ ልኖር ለክብርህ ዘመኔን በቃ ልሰጥህ

የፍቅር ምላሼ ሊሆንህ ደስ እንዲልህ ብዬ

እጆቼን አንስቼ መጣሁ እሄውልህ ውዴ

ተረቱን ተረቱን ንቄ ወደ አንተ ስመጣ

አንተን አይቼ እንጂ ኢየሱስ ሌላ ምን ፍለጋ (፭x)

አልገባኝም ነበር እኔ ያኔ ስትጠራኝ

እወድሃለሁ እኔ ስትለኝ መች እንዲህ መሰለኝ

ፊትህ ላይ እያነበብኩ ውዴ የፍቅር ፈገግታ

ኢየሱስዬ ብዬ ወዲያው እጄን እስካነሳ

አሳየኸኝ የፍቅር ፊትህን

መቼም ቢሆን እኔ አልለይህ

ኢሄውና መላ ማንነቴ

ንገሥበት ኢየሱስ አባቴ

ኢየሱስ አንተ የኔ ኢየሱስ

በአንተ አይደል ይህን ክብር ያየሁት

በእኔ ላይ ልቤን ሌላ ትምከት

አይሞላም ኢየሱስ የኔ አባት

የራሴ ትምክት እንዳይኖረኝ

ምህረትህ እኔን ሰው አደረገኝ

ትላንትን ሳየው ዛሬ ሆኜ

አንተ ነህ እዚህ ለመድረሴ (፬x)

ለዓለም የቀረ ቦታ እስካይኖረኝ

የፍቅሬን በኩር እንካ የልቤን በኩር እንካ

ለራሴ የቀረ ቦታ እስካይኖረኝ

የፍቅሬን በኩር እንካ የልቤን በኩር እንካ

ለክብርህ የቀረ ቦታ እስካይኖረኝ

የክብሬን በኩር እንካ ውሰደው እንካ እንካ

የአንተ ነው እንካ እንካ ያነጠፍኩልህ እንካ

ተራመድበት እንካ ወደ እኔ ናበት እንካ

ኦ የፍቅሬን በኩር እንካ ውሰደው (፬x)

(ውሰደው) ኢየሱስ አንተ የኔ ኢየሱስ

(ውሰደው) በአንተ አይደል ይህን ክብር ያየሁት

(ውሰደው) በእኔ ላይ ልቤን ሌላ ትምከት

(ውሰደው) አይሞላም ኢየሱስ የኔ አባት

(ውሰደው) የራሴ ትምክት እንዳይኖረኝ

(ውሰደው) ምህረትህ እኔን ሰው አደረገኝ

(ውሰደው) ትላንትን ሳየው ዛሬ ሆኜ

አንተ ነህ እዚህ ለመድረሴ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ