አለ ከእኔ ጋር
Ale Kenie Gar
2011 · ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የትላንቱን ነገር ጌታዬ ካስረሳኝ
አምናን አሳልፎ ለዛሬ ካበቃኝ
ስለነገው ደግሞ አምኜ ልናገር
አዝማች · Chorus
አለ ከእኔ ጋራ ከቶ የማይደክመው ስለእኔ ሚናገር (፫x)
አለ ከእኔ ጋራ ከቶ የማይደክመው ስለእኔ ሚናገር (፪x)
አለ እግዚአብሔር አለ
አለ መንፈስ ቅዱስ አለ
አለ የሚመራኝ አለ
አለ የሚራራልኝ አለ
አለ አለ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እረኛ እንደሌለው አልቅበዘበዝም
በሚነፍሰው ንፋስ አልነዋወጥም
መሠረቴ ጽኑ እንደሆነ አውቃለሁ
አዝማች · Chorus
የማመልከው አምላክ የተናገረውን/የተናገረኝ ሲያደርግ አይቻለሁ (፪x)
የማመልከው አምላክ የተናገረኝ ሲያደርግ አይቻለሁ (፪x)
አለ እግዚአብሔር አለ
አለ መንፈስ ቅዱስ አለ
አለ የሚመራኝ አለ
አለ የሚራራልኝ አለ
አለ አለ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እንዳለኝ እኖራለሁ እንደተናገረኝ
የምትረግጠው ምድር ያንተ ነው እንዳለኝ (፪x)
እንደንስር በሰማይ በከፍታ እበራለሁ
እንደአንበሳ ደቦል በምድር እመላለሳለሁ
እመላለሳለሁ (፫x) ከልካዬ ኧረ ማነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ