ጌታ ተናግሯል
Gieta Tenagrual
2011 · ትራክ 7 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰማይን ይሁን ያለው ማነው እግዚአብሔር ነው
ምድርን ይሁን ያለው ማነው የእኔ አባት ነው
ታዲያ እኔ ለምን እጨነቃለሁ ዝም ብዬ እዘምራለሁ አሃ
ታዲያ እኔ ለምን እጨነቃለሁ በደስታ እዘምራለሁ አሃ
ቁጥር 2 · Verse 2
እርሱ ተናግሯል በሕይወቴ ላይ
የሚቀር የለም ሁሉም ይሆናል
ጌታ ተናግሯል ቤተሰቤ ላይ
የሚቀር የለም ሁሉም ይሆናል
ጌታ ተናግሯል በሃገሬ ላይ
የሚቀር የለም ሁሉም ይሆናል
ቁጥር 3 · Verse 3
እግዚአብሔር በማን ይመሰላል ከማን ጋራ ይወዳደራል
የሁሉ ፈጣሪ ነው ኃይሉ እጅግ ታላቅ ነው
ጐበዝ ነን ያሉ ይወድቃሉ ኃይለኞች ደግሞ ይደክማሉ
ጌታን መመኪያ ያደረጉ ሕይወታቸውን ለርሱ የሰጡ
ይወጣሉ ይሮጣሉ ፣ ከቶ አይደክሙም ያሸንፋሉ
ከፍታውን ይይዛሉ
አዝማች · Chorus
እወጣለሁ ገና ፣ እሮጣለሁ ከቶ አልደክምም አሸንፋለሁ
ከፍታውን እይዛለሁ
እይታዬ እግዚአብሔር ነው የእኔስ ኑሮ ሰማያዊ ነው
አምኖ በምድር አሰማርቶኛል ማንነቴን ተርክ ብሎኛል
ለተጠማ እርካታ ለደከመው ጉልበት ላዘነው ደስታ
ይህን እንደሚሰጥ ነው ማውቀው የእኔ ጌታ (፪x)
አዝማች · Chorus
ይሄ ነው የተጻፈው
ይሄ ነው ለእኔ የተባለልኝ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ