ያየሁትን
Yayehuten
2011 · ትራክ 3 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ከአንተ ወዴት ወደማን ወዴት እሄዳለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ድምጽህን ሰምቼ አንዴ ተደላድያለሁ
የሕይወት ቃል አለ በአንተ ሕይወት አግኝቻለሁ
ሰለቸኝ ደከመኝ አታውቅ እኔ አይቼሃለሁ
ታዲያ ከእቅፍህ ወዴት ወዴት እሄዳለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
አባት ቢሉት የደረሰላቸው
ፍቅር ሚሉት የቀመሱት ናቸው
ተስፋ ጠፍቶ ተስፋ የሆናቸው
በተዐምራት በድንቅ የመራቸው
አመስግኖ አይጠግብም ልባቸው (፪x)
አዝማች · Chorus
ክበር ብሎ ንገሥ ብሎ (አሜን)
ልዩ ብሎ አይጠግብም ልባቸው (፪x)
ያየሁትን የሰማሁትን (የሰማሁትን)
እናገራለሁ ያረፍኩበትን (ያረፍኩበትን) (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሞተና በሶስተኛው ቀን ተነሳና
ሞተና በሶስተኛው ቀን ተነሳና
ነፃ አደረገኝ ዕዳዬን ከፈለና
ቀኑን ሙሉ በፍቅርህ በቤትህ እኖራለሁ (፪x)
በሚያስተማምነው ክንድህ በእርሱ ላይ አርፌአለሁ
በውኃ ዳር እንደአለች ተክል ፍሬያማ ሆኛለሁ
የረገጥኩት ምድር በአንተ ሲገዛ አይቻለሁ
ስምህን ጠርቼ ጌታ መቼ አስነካለሁ
አዝማች · Chorus
ያየሁትን የሰማሁትን (የሰማሁትን)
እናገራለሁ ያረፍኩበትን (ያረፍኩበትን) (፪x)
ሞተና በሶስተኛው ቀን ተነሳና
ሞተና በሶስተኛው ቀን ተነሳና
ነፃ አደረገኝ ዕዳዬን ከፈለና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ