ካወቅሁት ጀምሮ
Kaweqhut Jemero
2011 · ትራክ 11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እኔ ያወቅሁት ካወቅሁት ጀምሮ
ታሪክ ሲለውጥ በአዲስ አሳምሮ
ሰዎችም ሲሉ ሃዘኔን አስረሳኝ
የጌቶች ጌታ ነው የይሁዳ አንበሳን
አዝማች · Chorus
እያሉ ሲመሰክሩ ፣ ጌታ ነው ይክበር እያሉ
እያሉ ሲመሰክሩ ፣ አዳነኝ ነው ይክበር እያሉ
እያሉ ሲመሰክሩ ፣ ልዩ ነው ይክበር እያሉ
እያሉ ሲመሰክሩ ፣ አወጣኝ ከእሳት እያሉ
ማን ያልወጣ አለ ከጭንቅ ከፍራቱ
አንተን አስገብቶ ጌታ በሕይወቱ
ተዐምረኛ ሃይለኛ ነህ የተጣለውን ታነሳለህ (፫x)
ተአምረኛ ሃይለእኛ ነህ በፍቅር ልብን ትይዛለህ
ቁጥር 2 · Verse 2
የታሰርኩበትም ሰንሰለት ረገፈ
የእስር ቤቱ መዝጊያ ራሱ ተከፈተ
አዳነኝጌታዬ መልአኩን ልኩ
ነፍስም አልቀረኝ አይ አደራረጉ
አዝማች · Chorus
እያሉ ሲመሰክሩ ፣ ጌታ ነው ይክበር እያሉ
እያሉ ሲመሰክሩ ፣ አዳነኝ ነው ይክበር እያሉ
እያሉ ሲመሰክሩ ፣ ልዩ ነው ይክበር እያሉ
እያሉ ሲመሰክሩ ፣ አወጣኝ ከእሳት እያሉ
ማን ያልወጣ አለ ከጭንቅ ከፍራቱ
አንተን አስገብቶ ጌታ በሕይወቱ
ተዐምረኛ ሃይለኛ ነህ የተጣለውን ታነሳለህ (፫x)
ተአምረኛ ሃይለእኛ ነህ በፍቅር ልብን ትይዛለህ
ቁጥር 3 · Verse 3
እንደእግዚአብሔር ያለ ማንም የለ እያሉ
ወንድሞች በሆታ ስራህን ያወራሉ
እንደእግዚአብሔር ያለ ማንም የለ እያሉ
እህቶች በዕልልታ አንተን ያደንቃሉ
ፍቅርህን የቀመሱ በረከትህን ያዩ
ከውስጥ ከልባቸው አንተን ያከብራሉ
አንተን ያከብራሉ አንተን ያነግሳሉ
ቅዱስ ነህ እያሉ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ