Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በማለዳ ምሥጋናዬ

Bemaleda Mesganayie

2011 · ትራክ 4 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በማለዳ ምሥጋናዬ በሌሊትም ዝማሬዬn

ይዤ ልቅረብ ወደ ፊትህ

ቤትህን ይሙላው ያውድልህ (፪x)

ሰዎች ሰውን አይተው ያፈገፍጋሉ

የሕይወትን መንገድ ጥለው ይሄዳሉ

እኔ ግን ባሰብኝ ጨመረብኝ ፍቅሩ

አልሻም ለሰከንድ መውጣት ከድንበሩ

አልሻም ለሰከንድ መውጣት ከድንበሩ

እልሻም ለሰከንድ መውጣት ከክልሉ (፪x)

በማለዳ ምሥጋናዬ በሌሊትም ዝማሬዬ

ይዤ ልቅረብ ወደ ፊትህ

ቤትህን ይሙላው ያውድልህ (፪x)

በምድር እስካለሁ እኔ እናገራለሁ

ብዙ ተደርጐልኝ ብዙ አይቻለሁ

የማይገባኝን ሆኖልኝ እያየሁ

ክብር ለሚገባው ክብር ይሁን እላለሁ

ጐንበስ ቀና ብዬ አመልከዋለሁ (፬x)

እኔስ (፬x) እኔስ እንደገና ቃልን እገባለሁ

ሃሳብህን ይዤ ሃሳቤን እጥላለሁ

የወደድከው ይሁን አባ እኔ እኔ እታዘዛለሁ

አንተን ደስ ካለህ ሌላ ሌላ ምን እፈልጋለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ