የእግዚአብሔር ጊዜ
Yegziabhier Gizie
2011 · ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የእግዚአብሔር ጊዜ የተወደደ
ደረሰ ለእኔ እርሱ የፈቀደው
የማጨድ ጊዜ የመከር ዘመን
መጥቷል ከፊቴ የመከናወን (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ያለው ይሆናል
አትችልም አይሆንም የሚለው የታል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዘመን መጣ ለእኔ (፰x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ያላየሁትን ባይኔ የማይበት ያልሰማሁትን የምሰማበት
በህልውናው ምጥለቀለቅበት ክብሩን እያየሁ የማመልክበት (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ይሆናል ያለው ይሆናል
አትችልም አይሆንም የሚለው የታል (፪x)
ከላይ ከላይ ከላይ ከላይ (፪x)
ምህረቱን ለእኔ ሊያሳይ መንፈሱ መጣ ከላይ ከላይ (፪x)
ከላይ ከላይ ከላይ ከላይ (፪x)
ምህረቱን ለእኔ ሊያሳይ አባቴ መጣ ከላይ ከላይ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
እኔ የሚገርመኝ እኔ የሚደንቀኝ
ይህ ግዙፍ ሰማይ ይህ ግዙፍ ምድር
ሌላ አልተናገርክ ሌላ አላልካቸው
በአንድ ቃል ብቻ አጸናሃቸው (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ያለው ይሆናል
አትችልም አይሆንም የሚለው የታል (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ሌሊቱን ሙሉ ቢጥር ቢደክም
መረቡ ባዶ ዓሣ የለውም
ኢየሱስ መጥቶ ካልተናገረው
ፈቀቅ በልና ወደጥልቁ ጣለው (፪x)
እንዳለው መረቡ ሞላ
ተዐምር ነው ድንቅ ነው የሰራው ስራ (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ከላይ ከላይ ከላይ ከላይ (፪x)
ምህረቱን ለእኔ ሊያሳይ መንፈሱ መጣ ከላይ ከላይ (፪x)
ከላይ ከላይ ከላይ ከላይ (፪x)
ምህረቱን ለእኔ ሊያሳይ አባቴ መጣ ከላይ ከላይ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ