አሳርፈኸኛል
Asarefehegnal
2011 · ትራክ 9 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንዲህ አልነበረም ታሪኬ
አንተ ሳትገባ በሕይወቴ (፪x)
ውስጤን ስትነካው ታወቀ በፊቴ
አሳርፈኸኛል ኢየሱስ መድኃኒቴ (፪x)
አዝማች · Chorus
አንተ ነህ ትምክህቴ ውበት ደም ግባቴ
አመሰግናለሁ ተመስገን አባቴ (፪x)
ምህረትህ ቸርነትህ ሁልጊዜ ይከተሉኛል
ዘለዓለም በቤትህ ያኖሩኛል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝ አንድም ነገር የለም
በለመለመው መስክ ይመራኛል በእረፍት ውኃ ዘንድ ያሳድረኛል
ነፍሴን መለሳት ስለስሙ በጽድቅ መንገድ መራኝ
በሞት መሃከል እንኳን ብሄድ
እርሱ ከእኔ ጋር ነውና ክፉን አልፈራም እኔ አልፈራም
ለእኔ ያደረገው የሆነው
ይህ ነው አይባልም ብዙ ነው (፪x)
እኔ ነፃ እንድሆን ሁሉን ሆኖልኛል
ሞቴንም በሞቱ ጌታዬ ለውጧል (፪x)
አዝማች · Chorus
አንተ ነህ ትምክህቴ ውበት ደም ግባቴ
አመሰግናለሁ ተመስገን አባቴ (፪x)
ምህረትህ ቸርነትህ ሁልጊዜ ይከተሉኛል
ዘለዓለም በቤትህ ያኖሩኛል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ