Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አልፈራም

Alferam

ትራክ 8 · 6:26 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እኔ የማመልከው ወረትን አያውቅም (፪x)

እውነተኛ ፍቅር አለው ለሰው ልጆች (፬x)

ነፍሴ ወዳዋለችና ይሄንን ጌታ

ሁሌ ታመልከዋለች ጠዋትና ማታ (፪x)

ነፍሴ እንደዋላ አንተን ተጠማች (፪x)

መንፈሴም በውስጤ አንተን አለች

ሥጋዬም ሁልጊዜ አንተን ናፈቀች (፪x)

ኢየሱስ እርካታ ነህ

ኢየሱስ እረፍቷ ነህ

ኢየሱስ ሰላሟ ነህ

ለእርሷ ፍቅር ያለህ (፪x)

ሁልጊዜ አንተን ትላለች በፍቅርህም ተይዛለች

ያለ አንተ አይሆንላት እረዳት ስለሆንካት (፪x)

እረዳት ስለሆንካት ፣ እረዳት ስለሆንካት (፪x)

ከምወድህ በላይ ነህ

ከማፈቀርም በላይ

ከተገመትከው በላይ ነህ

ከተባለልህ በላይ ነህ (፪x)

ኢየሱስ ልዩ ነህ ኢየሱስ

ኢየሱስ ድንቅ ነህ ኢየሱስ

ኢየሱስ ትልቅ ነህ ኢየሱስ

ኢየሱስ ኃያል ነህ ኢየሱስ

ብቻህን ድንቅ የምትሰራ

ልጆችህን የምታኮራ

ዘወትር ነህ ከእኔ ጋራ

አንተን ይዤ እንደምን ልፍራ (፬x)

አልፈራም ብርቱ ጌታ ስላለኝ አልፈራም

አልፈራም ኃያል ጌታ ስላለኝ አልፈራም

አልሰጋም ብርቱ ጌታ ስላለኝ አልሰጋም

አልሰጋም ኃያል ጌታ ስላለኝ አልሰጋም

አልፈራም ብርቱ ጌታ ስላለኝ አልፈራም

አልፈራም ኃያል ጌታ ስላለኝ አልፈራም

አልፈራም (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ