ብሩክ ሥምህ ይባረክ
Beruk Semeh Yebarek
ትራክ 3 · 7:03 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አቤቱ አቤት አቤቱ አቤት
አንተ ነህ አንተ አንተ ነህ አንተ
ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ሆነህ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ተራሮች ሳይወለዱ ምድርም ሳይሠራ
ዓለማት ሳይፈጠሩ አንተ ግን አንተ ነህ (፪x)
ተራሮች ሳይወለዱ ምድርም ሳይሠራ
ዓለማት ሳይፈጠሩ አንተ ግን አንተ ነህ
ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን
እንደ ሌሊትም ትጋት ነውና (፪x)
ዘመናትም የተናቁ ይሆናሉ
በማለዳ እንደ ሣር ያልፋሉ
ማልዶ ያብባል ያልፋል
በሠርክም ጠውልጎና ደርቆ ይወድቃል (፪x)
አዝማች · Chorus
አቤቱ አንተ ብርቱ ነህ ዕውነትህም ይከብብሃል (፪x)
የባሕርንም ኃይል አንተ ትገዛለህ (፪x)
የሞገዱንም መናወጥ አንተ ዝም ታሰኘዋለህ
የሞገዱንም መናወጥ አንተ ዝም ታሰኘዋለህ
አቤቱ ከአማልክት የሚመስልህ የለም
እንደ ሥራህም ያለ የለም (፬x)
አቤቱ ከአማልክት የሚመስልህ የለም
እንደ ሥራህም ያለ የለም (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ያደረካቸው አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ
አቤቱ በፊትህም ይሰግዳሉ ሥምህን ያከብራሉ
አቤቱ በፊትህም ይሰግዳሉ ሥምህን (ያከብራሉ)
አቤቱ ድንቅን የምታደርግ አንተ ታላቅ ነህና
አንተ ብቻህን ታላቅ ታላቅ አምላክ ነህና (፪x)
አምላክ ሆይ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ
ይኖራል ይኖራል
አዝማች · Chorus
የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው (፬x)
በበረከትና በምሥጋና ሁሉ ላይ
ከፍ ከፍ ያለው ስምህ ብሩክ ስምህ ይባረክ (፬x)
በበረከትና በምሥጋና ሁሉ ላይ
ከፍ ከፍ ያለው ስምህ ብሩክ ስምህ ይባረክ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከሥም በላይ ሥም ይዘሃል
ጌታ ኢየሱስ አንተን ከቶ ማን ይመስልሃል
ማን ይመስልሃል (፪x)
የፀና ብርቱ ግንብ ነው
ከሁሉ በላይ ኃይል አለው
የፃድቃን መክበሪያ ማምለጫ ዓለት ነው
ሥምህ ጉልበት ነው
የፀና ብርቱ ግንብ ነው
ከሁሉ በላይ ኃይል አለው
የፃድቃን መክበሪያ
ማምለጫ ዓለት ነው ሥምህ ጉልበት ነው (፭x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ