Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ውለታህ

Weletah

ትራክ 4 · 4:18 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ውለታህ ውለታህ

ከአዕምሮዬ በላይ ነው ነው አሃሃ (፫x)

ጌታዬ ውለታህ ከአዕምሮዬ በላይ

ኢየሱስ ውለታህ ከአዕምሮዬ በላይ (፪x)

ታላቅ ምሬቴ ለመልካም ሆነ

በአንተ ታሰብኩኝ ጭንቀቴ ቀረ

በጉብኝትህ ደስ አሰኘኸኝ

ታላቅን ነገር አደረግህልኝ (፪x)

አባቴ መልካም ነህ መልካም ለኔ አድርግ

ጌታዬ ድንቅ ነህ ድንቅን ለእኔ ሠርተሃል

እግዚኣብሔር ጻድቅ ነህ በጽድቅ መርተኸኛል

እንዳለ ግን በሕይወት መኖርን ሰጥተኸኛልና

ታዲያ ለዚህ ለውለታህ ምን እከፍልሃለሁ (፪x)

ባይመጥንም ምሥጋናዬ ሃሌሉያ ተመስገን እላለሁ (፪x)

ለውለታህ ጌታ የምከፍልህ አጣሁ

ለስጦታህ ኢየሱስ የምሰጥህ አጣሁ (፪x)

ባከባብርህ ይሄ አይበቃህም

ባሞጋግስህ ይሄ አይበቃህም

ተመስገን ነው ያለኝ ተመስገን ነው ያለኝ

ተባረክ ነው ያለኝ ተባረክ ነው ያለኝ (፪x)

ቃላቶች ያጥሩኛል ለውለታህ ምላሽ

ኧረ ኢየሱስ ለእኔ ነህ ደራሽ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ